ዐቢይ ይልማ
መምህርና ጋዜጠኛ | |
የተወለዱት | 1973 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ |
---|---|
ዜግነት | ኢትዮጵያዊ |
ባለቤት | ወ/ሮ ጥበብ ባህሩ |
ልጆች | ምራን ዐብይ |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና |
ዐቢይ ይልማ (በ1973 ዓ.ም ተወለደ) ኢትዮጵያዊ መምህር እና ጋዜጠኛ እንዲሁም የብዙ መጻሕፍት ደራሲ ነው።
እምቅ ጥበባቸውን በማውጣት ባላቸው ሙያ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በተለይም ወጣቱን የማህበረሰብ ክፍል በማንቃት በኩል የራሳቸውን ሚና እየተጫወቱ ካሉ ግለሰቦች መካከል የሚጠቀሰው መምህርና ጋዜጠኛ ዐቢይ ይልማ በአሁ ኑሰዓት በአሐዱ ሬዲዮ 94.3 ላይ ሣድስ በተሰኘ የሬዲዮ ፕሮግራም እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ በዩቲዩብ ቻናል Abiy yilma / Saddis Tv በተሰኘ የራሱ ቻናል ከ225,000 ሺዎች በላይ ተከታይ ኖሮት የሚሰራ የሚታወቅ ጋዜጠኛ ነው።
ዐቢይ ይልማ የሜሴንጀርስ ሙዚቃ ቡድን መስራች የሉሲፈር ተፋላሚ፡ የመንፈ-ሳይንሳዊ እውቀት መጋቢ፡ የዓለምን ስውር መንፈሳዊ አሻጥር አፍራሽ፡የዐዕምሮ ማሳጅ በተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራሙ ብዙዎችን ያፅናና፡ ድንቅ ጥበበኛ፡ መምህርና ጋዜጠኛ ነው።
ዐቢይ ይልማ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው መሳለሚያ በተባለ ሥፍራ 1973 ዓ.ም ተወለደ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በአስኳላ ትምህርት ገበታ ላይ በርካታ እውቀቶችን በልጅነት አእምሮው የቀሰመ ትንታግ ልጅ ሆኖ ነበር ያደገው። በአብነት ትምህርት እስከ ድቁና ድረስ ተምሯል። በቤተክክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ በርካታ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን ያስተማረ ጥበበኛ ሰውና ብስል ፍሬ ነው። በመንፈሳዊ ስነምግባር ያደገው ዐቢይ ገና በልጅነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ሳለ ነበር ስፍር ቁጥር የሌላቸውን መፅሐፎች ለማንበብና መንፈሳዊና ዓለማዊ እውቀቶችን ለመቅሰም የቻለው። በሀይማኖት ጉባኤዎች ላይ በርካታ ፅሑፎችን በማቅረብ የሚታወቅና ለቅድስት ቤተክርስቲያኗ አማኝ የማህበረሰብ ክፍሎች ሀይማኖታዊ አገልግሎቶችን ያበረከተው። በሰንበት ትምህርት ቤት እና በአስኳላ የነበረው አገልግሎትና ተሳትፎ ዛሬውን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት አስችሎታል።
ዐቢይ ከ12 ዓመቱ በኃላ፣ ወደ ውቢቷ ሐዋሳ ከተማ በማቅናት የከፍተኛና የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን በመምህርነት ሙያ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል። በኋላም ወደ ህንድ ሀገር ተጉዞ 2ኛ ዲግሪውን ፓሩል ዩኒቨርሲ ቲክሊኒካል ሳይኮሎጂ እንዲሁም በዚሁ በሀገሩ 2ኛዲግሪውን በMBAሰርቷል።
ዐቢይ ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ ለ16 ዓመታት የጤና ስቃይ ገጥሞት ነበር። ይሁን እንጂ እንደማንኛውም ሰው ታምሜያለሁና ከእንግዲህ አልተርፍም ብሎ ተስፋአ ልቆረጠም፣ በፍርሃት አልተሽመደመደም ።እንዲያውም እየሞተ ዳነ እንጂ። በአንጀት አካባቢ በተፈጠረ ህመም በሆስፒታል አስተኝቶት ያውቃል። የቀዶ ህክምና ተደርጎለት ሳይነቃ የቆየበትም አጋጣሚም ነበር። ይህ የበሽታ ዝርያ በአብዛኛው ገና በተወለዱ ሕፃናት ላይ ነው የሚከሰተው። ነገር ግን ከ1000 አንድም በታዳጊ ልጆችም ላይ መከሰት ይችላል። በሳይንሳዊ አጠራሩ ሐይፐርትሮፊክ ፓይሎሪክ ስቴኖሲስ (Hypertrophicpyloricstenosis) ነው የሚባለው። ችግሩ የሚከሰተው የምግብ መፍጫ የሆድ እቃችን ትልቁ ጨጓራ ብለን የምንጠራው ክፍል ታችኛው፣ ወደ ትንሹ አንጀት መግቢያው ላይ ነው። ልክ የብር መጠቅለያ ላስቲክ እንደሚለጠጥ፣ እንደሚሰበሰብ አይነት ተፈጥሮ ያለው ጡንቻ እዚህ ክፍል ላይ አሉ። ፓይሎሪክ ስፊንክተር (pyloricsphincter) ይባላል። ቢሆንም እርሱ በፈጣሪው የሚያምን መንፈሰ-ጠንካራ ሰው ነበር። የስጋውን ድክመት ተጠቅሞነ ፍሱን አጠንክሯታል። በየሚኒሚዲያው ላይ ህመሙን ቃልና ሀሳብ እያሸከመ ስቃዩን ዘምሮበታል!ፅፎበታል። ኪነት ተጫውቶበታል። ልጅነቱን በአግባቡ መጠቀም የቻለ፤ እያንዳንዱን እርምጃውን በአንክሮ የተመለከተ ዓይኑ በውበት ልቡ በትቢት ያላሸነፈው ጨዋታ ያላታለለው ያገኘው ዕድል በአግባቡ የተጠቀመ አወይ ልጅነቴ ነፍስ አለማወቄ ሲገረድፉልኝ አለመሳለቄ ብሎ ያልተቆጨ ጥንቁቅ ሰው ነው።
መምህርና ጋዜጠኛ ዐቢይ ይልማ ከወ/ሮ ጥበብ ባህሩ ጋር ትዳር በመመስረት ምራን ዐብይ የተባለ አንድ ወንድ ልጅ አፍርቷል።
ዐቢይ ይልማ በተለያዩ ቦታዎች በመምህርነት ሙያ ከ10 ዓመታትበላይ አገልግሏል።
ዐቢይ በመምህርነትና በጋዜጠኝነት ሙያው መሸጋገሪያ ወቅት ደግሞ ሜሴንጀርስ የተሰኘ የሙዚቃ ቡድን አቋቁሞ ቶክቻውንና ሙሉዓለም ሽፈራውን ይዞ ለዓመታት በዝነኛ የሙዚቃ ሥራዎቹ ዘልቋል። የራሱ የሆነ ነጠላ ዜማም የለቀቀ ድምፃዊ ነበር። ጅማሮውን በሐዋሳ ያደረገው ሜሴንጀርስ በአዲስአበባ ተገኝቶ በአለቤ ሾው ቃለመጠይቅ ተደርጎለት በኋላም በዚሁ በአዲስአበባ መቀመጫውን አድርጎ በአለቤ እየተመራ ስመ ገናና ለመሆን ችሏል። ይሁን እንጂ ዐቢይ የሙዚቀኞችን ህይወት በጥልቀት ከገመገመ በኋላ አዝማሚያው ስላላማረው እራሱን ገታ አድርጎ በማሰብ ወደሚወደው የመምህርነት ሙያው ለመመለስ ወስኖ አስተምሯል። በዚህ መካከል በአንድ አጋጣሚ የሀገሩን ኢትዮጵያ ምድር ለቆ ሰማይን ተሰንጥቆ ማረፊያውን ፈረንሳይ ለማድረግ ቆርጦ እየተንቀሳቀሰ ሳለ በመንፈሳዊም ሳይንሳዊም ስለነበር በሀገሩ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት አልጥምህ ያለው ጉዳይ ፈረንሳይ ሲደርስ የባሰ ሆኖ አገኘው። ወጣቱ በተለያየ መንገድ ወደጥፋት እየሄደ እና አዘቅት ውስጥ እየሰመጠ እንደሆነ የተረዳው ዐቢይ ለጥፋት የዳረጋቸው ምስጢር ምን እንደሆነ መመርመር ያዘ። በምርምሩ ምስጢራዊ ሰነዶችንና መረጃዎችን ሲያገኝ ያገኛቸውን መረጃዎች በመያዝ ጉዳዩ የአንዲት ኢትዮጵያ ወይም ፈረንሳይ ሳይሆን ዓለም የተዘፈቀበት ነው ሲል የሀገሩን ወጣቶች ለመታደግና ለማስተማር ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ተመልሶ ትምህርቶችን አስተምሯል። እያስተማረምይገኛል።
ከመምህነቱ ጎንለጎን በጋዜጠኝነት ሙያ ሐዋሳ በሚገኘው በደቡብ ኤፍ.ኤም 100.9 ቀጥሎ በሻሸመኔ ፋናኤፍ.ኤም 103.4 እና አሁን ላይ ደግሞ በአሐዱ ሬዲዮ 94.3 ላይ በድምሩ ከ18 ዓመታት በላይ ያገለገለ እና እያገለገለ ያለ የሀገር ልጅ ነው።
ቀልጣፋው፣ አንደበተ ርትኡ፣ መምህሩና ጋዜጠኛው ዐቢይ ይልማ ዛሬ ላይ ዓለም ፈጣሪውን ገድሎ እራሱ በተመቸው መልኩ ፈጣሪውን እየሰራ/እየፈጠረ ባለበት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ብቻውን መመለክ በጀመረበት ስውርፀረ-ሐይማኖታዊ ንቅናቄ በተስፋፋበት በአሁኑ ወቅት ላይ ዐቢይ የራሱን ወጥ የሆነ አቋም ይዞ ሳይንስና ሐይማኖትን አስታርቆ ለወጣቱ በማስተማር ከማይታይ የአውሬ መንፈስ ጋር ጦርነትገ ጥሞ እየተፋለመ ያለ ጥበበኛ ጋዜጠኛነው። መምህሩ በርካታ ወጣቶች እራሳቸውን ካስገቡበት ማጥ እንዴት ማውጣት እንደሚችሉ እና እንዴትም መግባት እንደ ማይችሉ ቁጭ ብሎ በሳይንሳዊ፣ በመንፈሳዊ፣ በሳይኮሎጂካዊ መንገድ (መንፈሳይንሳዊ) መንገድ አፅንኦት ሰጥቶ ያስረዳል። በአሁኑ ሰዓትም (ከዓመታትበፊት) ይሰራቸው የነበሩ በተቋማት ውስጥ ማስተማርና የሙዚቃ ሥራዎቹን ሙሉ በሙሉ አቁሞ ጋዜጠኝነቱ ላይ አተኩሮ እየሰራ ይገኛል። ሣድስ የሬዲዬ እና የዩቲዩብ ፕሮግራሞቹ በአሁኑ ሰዓት በአሐዱ ሬዲዮና በዩቲዩብ ገፅ ላይ እጅግ ተፅእኖ የፈጠረ ፕሮግራም ነው።
በመንፈ-ሳይንሳዊ ይዘት ማለትም (በመንፈሳዊና ሳይንሳዊ-ሜታፊዚካል) ፎርማት በጠቅላላ እውቀትና ሥነ-ምግባር ዙሪያ ያተኮሩ ትንተናዎችንም ይሰራል። በአእምሮ ማሳጅ (የሳይኮሎጂካል) አነቃቂ ፕሮግራሞች ሚሊየኖችን ከጭንቀት፣ ከድክመት፣ ከድህነት፣ ከተዛነፈ የራስ ግምት እና ከመንፈሳዊ ውድቀት በማንሳት የተሻጋሪነትን ኃይል አጎናፅፏል። በዚህም የተጨበጠ ለውጥ ምክንያት ሚሊየኖች በፍቅር የሚወዱት የሚዲያ ዝግጅትነው። በፀረ-666 መረጃዎችን መምህር ዐብይ ይልማ ተለይቶ ይታወቃል። በተለይም በዚህኛው ዘመን ላይ የሚስተዋሉ እንደ ግብረሰዶምና መሰል ማህበራዊ ኪሳራዎች በምስጢረኛው የ666 ማህበረሰብ ደባ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆን ተብሎ እየተስፋፉ ይገኛሉ ሲል መምህር ዐብይ ይልማ ያምናል። በዚህም የተነሳ የዚህን የሚስጥረኛውን ማህበረሰብ ስውር ደባዎች በማጋለጥ ሚሊየኖችን ወጣቶች እየታደገ ይገኛል። በዘመን ፍፃሜ (Apocalyptic) ትምህርቶች ተለይቶ ይታወቃል። መምህርና ጋዜጠኛ ዐብይ ይልማ በርካታ ፕሮግራሞችን የሰራ ሲሆን በዚህ የሉሲፈር ወጥመድ ውስጥ ወድቀው የነበሩና አሁን እያገገሙ ያሉ ሰዎችን በፕሮግራሙ ላይ በቀጥታ በመጋበዝ ልምድ እንዲያጋሩም ያደርጋል። በዚሁ በእኛው ሀገር መዲናችንን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ መንፈሱ መኖሩን ያረጋገጠ ሲሆን ለዚህ መንፈስ ማፍረሻ የፊርማ ማሰባሰብ መርሃ ግብር እንደሚጀምርም በሚያስተምርበት በአንድ ወቅት ተናግሯል። መንፈሱ በሽታዎችን በማስፋፋት በርካታ የሰው ልጅ ቁጥርን የመቀነስ ዓላማ ስላለው ሀገራት እራሳቸውን እንደ ጦርነትና በሽታ ባሉ ሁኔታዎች ይዘፈቃሉ የሚለው ዐብይ ይልማ የዓለም መንግስታት ፍጥጫ እና የዓለም ፍፃሜ ትንቢትን የኢትዮጵያ ተሳትፎ፣ አውሮፓን ካናወጠው አዲሱ ኮቪድ (ኦሚክሮን) ጀርባ ያለው የክፋት አሻጣር፣ ማይክሮችፕ፣ የዓለም የህክምና ስርዓት፣ WHO እና ሌሎችም እጅግ በርካታ ፕሮግራሞችን ሰርቶ አስተምሯል።
"ዕውቀት ታላቋን ታከብራለችሚ! ዲያሀገርይገነባል!" በሚል አባባሉ የሚታወቀው ዐብይ ይልማ በጋዜጠኝነት ሙያው ወቅት እጅግ እየተነበቡ ያሉ አራት መጻሕፍትን ፅፎ ለአንባብያን አድርሷል።
- ፀረ-666 የተባለ መፅሐፍ የአዲሱ የዓለም ስርዓት አውሬው ገዢ መናፈስት የሚናገር።
- ሣድስ የጠቅላላ ዕውቀት መፅሐፍ (ይህ ፅሑፍ በወጣበት ወቅት ) 10ኛ ዙር እትም ላይ ይገኛል። ለምሳሌ: የአትላንቲክ ውቅያኖስ ጥንት የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይባል እንደነበር በማስረዳት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃ መረጃውን በብዙ ጥናታዊ ትንተናዎች ይዞ የመጣ የሚዲያ ባለሙያ ያደረገውን ጽሑፍ የተካተተበት መፅሐፍ ነው።
- "አልፈራም" - ፍርሃትን መቆጣጠሪያ የመንፈሳይንሳዊ መጽሐፍ ነው። በአእምሮ ማሳጅ አነቃቂ ትምህርቶቹ ላይ መሰረት ያደርጋል። በገበያላይይገኛል።
- ፀረ-666 ቁጥር 2 መንፈሳዊ ጦርንነት ውስጥ ነን፡፡ የተባለ መፅሐፍ ለገበያ አቅርቧል፡፡