Jump to content

ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሣ

ከውክፔዲያ

ዐብዱልጀሊል ዐሊ ካሣ (ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሣ)

በደቡብ ወሎ ቦረና ወረዳ መካነ-ሠላም ከተማ በህዳር 18/1977 ዓ.ም ከአባቱ ከሸኽ ዐሊ ካሣና ከእናቱ ከወይዘሮ አመተልመሊክ ዑምር ሙሐመድ ተወለደ።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቦረና 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። ከ9-10ኛ ክፍል በቦረና ከፍተኛ ትምህርት ቤት፣ ፕሪፓራቶሪ ትምህርቱንም እዛው ቦረና ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተከታትሎ በ1998 ዓ.ል ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ በ2000 ዓ.ል በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ድግሪውን በማዕረግ ተመርቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ተከታትሏል፣ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በደቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ድግሪውን (ኤም ኤ ድግሪ) ሲይዝ በ2009 ዓ.ል ጣልያን አገር ሄዶ ሎምባርዲያ ሪጅን ከሚገኘው ብሬሽያ ዩኒቨርስቲ በኢንተርናሽናል ቢዝነስ ሌላ ተጨማሪ ማስተርስ ድግሪ ተመርቋል።በክንፈ የደህንነት ማሰልጠኛ ተቋም ከሰለጠነ በኋላ በቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በኢኮኖሚ ደህንነት ክፍል፣ በታክስ ኢንቨስትጌሽን ክፍል ለስምንት አመታት ሰርቷል።

ኪነት ያገነነው አጼ የሚለውና በ2010 ዓ.ል የታተመው መጽሐፉ በአገሪቱ በብዙው የተወራለትና መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀ ሲሆን ተምኔታዊት ደሴት የሚለው ጥነታዊ መጽሐፉ ደግሞ ሁለተኛው መጽሐፉ ነው።