ዘመነ ህዳሴ

ከውክፔዲያ

ዘመነ ህዳሴ (Renaissance ረኔሳንስ ) በተለይ በአውሮፓ ታሪክ እንደሚወሰን ከ1445 እስከ 1640 ዓም ድረስ ያህል ያለው ጊዜ ነው። በተለይ በዚህ ዘመን የተከሠተው የሥነ ጥበብ ተሃድሶ ማለት ነው።

ይህም ቁስጥንጥንያኦቶማን ቱርኮች ከወደቀበት ዓመት ከ1445 ዓም ጀምሮ አካባቢ ይቆጠራል። በዚያን ጊዜ ቢዛንታይን መንግሥት ስለ ወደቀ የአውሮፓ ሥነ ጥበብ ማዕከል ወደ ጣልያን ሊዛወር ጀመረ። ከዚህም በኋላ የሥነ ጥበብ «ዘመነ ህዳሴ» ከጣልያን ወደ ሌሎቹ አውሮፓ አገራት ይስፋፋ ነበር።

«የፕሮቴስታንት ተሃድሶ» ንቅናቄ (Protestant Reformation) ደግሞ በዚህ ዘመን ያህል ውስጥ (ከ1509 እስከ 1640 ዓም ድረስ) ተከሠተ።