ዘረኝነት በሩሶ-ዩክሬንያን ጦርነት

ከውክፔዲያ
2022 Russian invasion of Ukraine.svg

የሩሶ-ዩክሬንያን ጦርነት በ የካቲት 24 2022 ዓም ሩስያ ዩክሬን ላይ ባደረገችው ወረራ ነው የተጀመረው። ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ዩክሬናውያንና ሌላ ዜግነት ያላቸው ስደተኞች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በዚህ ቀውስ ላይ ብዙ የምዕራብያውያን የዜና አውታሮች ስለ ዘረኝነት በማናፈስ የተሳሳተ መረጃ ዘግበዋል። የምዕራብያውያን መገናኛ ብዙሃን ይህንን የዘርኝነት ጥቃት "ሰማያዊ አይን እና ነጭ ቆዳ" ያላቸው የዩክሬን የአውሮፓ አርያን ዜጎች ብቻ ለጦርነቱ ሰለባ እንደሆኑ አዳልተው ዘግበዋል።

ሁነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ብዙ የማህበራዊ ገፆች እንደሚሉት ከሆነ በሩሶ-ዩክሬንያን ጦርነት ላይ የዩክሬን ህዝብን የሚደግፍ ዘረኝነት በምዕራብያውያን ሚድያ ተሰንዝሯል። ለምሳሌ "ሺባፎርኤቨር" የተባለ አንድ የትዊተር ተጠቃሚ አንድ የቢቢሲ ዘጋቢ ለምን ሰማያዊ አይን ያላቸው ነጭ ዩክሬናውያን የጦርነቱ ሰለባ እንደሆኑ በምሬት እንደገለፀ የምስል ማስረጃ ለቋል።

ዘ ሪፖርተርስ ለምን ወርቃማ ፀጉርና ነጭ ቆዳ ያላቸው የአውሮፓ ዜጎች በፑቲን ሚሳኤል ጥቃት ብቻ እንደሚዘገብ ምሬቱን ገልፅዋል። ሌሎች ገፆች እንደሚያመለክቱት እንደሆነ የምዕራብያውያኑ ሲቢሲ ዜና ዘጋቢ ዩክሬንን እንደ "ሰለጠነች" አፍጋኒስታንና ኢራቅን "ያልሰለጠኑ" ሀገራቶች ብሎ ትልቅ የዘረኝነት ጥቃት ሰንዝሯል። በዘገባው ላይ እንደተናገረው "ባሁኑ ጦርነት አንድ ሺህ የሚያክሉ ዪክሬናውያን ተሰደዋል። አሁን ተመልከቱ ሁላችንም [ምዕራባውያን] እንደ አፍጋኒስታንና ኢራቅ የተበላሸች ሀገር እንዳትሆን መጠንቀቅ ይገባናል" ብሏል። በመቀጠል "ይህች ሀገር በስልጣኔ ላይ ያለች ላይ የአውሮፓ ሀገር ናት። አላን ማክሊኦድ የተባለው የማህበራዊ ድህረገፅ ተጠቃሚ በአንድ ቪድዮ ላይ እዳወጣው "የዩክሬን ህዝብ ቅምጥል የሚገባው ህዝብ ነው። ልክ እንደ መካከለኛው ምስራቅ ና ሰሜን አፍሪካ መሆን የለበትም። የአውሮፖ ህዝብ መሀከለኛ ክፍል የሚገኝ ንፅህ ህዝብ ነው።" በማለት በአረብ አገራት ላይ የዘረኝነት ጥቃት ሰንዝሯል። ማክሊዎድም ቀጥሎ የፈረንሳዩን ቢኤፍ ኤም ቲቪ ጅዘጋቢ ቪድዮ በማሰማት "እስቲ አስቡት! በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓ ተወንጫፊ ሚሳኤል ባላት ዘመን እንደ አፍጋኒስታንና ኢራቅ ስትሆን? ብሎ ሌላኛውን ጥቃት ሰንዝሯል።[1]

ራይክስኮሚሳሪያት ዩክሬን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በ1940–1944 ዓም የቆየው ራይክስኮሚሳሪያት ዩክሬን የተባለው የናዚ ጀርመን ግዛት ዩክሬንን ከጀርመን የወጡ ጎቲክ ሰዎች መኖሪያ እንደሆነች ተናግረዋል። በይዞታቸው ናዚ ጀርመኖች የዩክሬንን አንጡር ሀብት ባለቤት በማድረግ የተለያዩ ስሞችን በጀርመን ባህል ስም አድርገዋል። ይህም የናዚ አስተሳሰብ ያላቸው ምዕራብያኑ በተደጋጋሚ ዩክሬንን "የጀርመን ምድር" አድርገው በመሳል ያሞካሿታል።[2]

  1. ^ https://www.opindia.com/2022/02/russia-ukraine-crisis-western-media-shows-racism/amp/
  2. ^ Wendy Lower, Nazi Empire-Building and the Holocaust in Ukraine, p. 161