Jump to content

ዘሪቱ ከበደ

ከውክፔዲያ
ዘሪቱ ከበደ

ዘሪቱ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ትታወቃለች።

የህይወት ታሪክ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዘሪቱ ከበደ የቀድሞ ዘፋኝ የአሁን ዘማሪ ስትሆን የተወለደችዉ በአዲስ አበባ በ1976 ዓ.ም ተወልዳለች ። ከህዝብ ጋር መጀመሪያ በስፋት የተዋወቀችዉ "እስኪ መላ በሉ የሐገር ልጆች ሁሉ "በሚል ለኤችአይቪ መከላከያ ከአንጋፋ አርቲስቶች ጋር በመጣመር በሰራችዉ ሥራ ነው ፣መዚቃዉን ያቀናበረዉ ኤልያስ መልካ ሲሆን ፣ከዘሪቱ በተጨማሪ ኢዮብ መኮንን በዘፈኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ አይን ዉስጥ ገብቷል ። ዘሪቱ ከበደ ከተወሰኑ ነጠላ ዜማዎች ዉጪ ፣በአልበም ደረጃ ያሳተመችዉ አንድ ብቻ ቢሆንም ያተረፈችዉ ተወዳጅነት ናዝና በፍጹም አንድ አልበም ብቻ ያለዉ አርቲስት የሚያገኘዉ አይደለም ፣ ከዛ የላቀ ነው ። አልበሟን ያቀናበረላት ኤልያስ መልካ ና ጓደኞቹ እነ ዘሩቤል ሞላ ከመንፈሳዊ አገልግሎት የመጡ ከመሆናቸዉ ባለፈ በነሱ ዘንድ ያየሁት እዉነተኛ የወንድማማች መዋደድ ፣ኢየሱስን ለመከተል ተጽዕኖ አሳድሮብኛል ፣ብላ ለዲጄ ፋትሱ በ VOA ጋቢና ፕሮግራም በተጋበዘችበት ወቅት የተናገረችዉ ዘሪቱ ፣ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ዘማሪነት ሕይወት ገብታ ሶስት መዝሙሮችን አቅርባለች ። ዘሪቱ ከበደ ገጣሚ የዜማ ደራሲ ና ድምጻዊት ከመሆኗም በተጨማሪ ፣ በተለያዩ ፊልሞችም ላይ ፣የተሰጧት ገጸ ባህሪዎች ተላብሳ በመተወን ብቃቷን አስመስክራለች ። የፈልም ማጀቢያ ሙዚቃዎችንም ሰርታለች ። በቅርቡ ያለፈዉና በኢትዮጵያ ሙዚቃ ትልቅ አሻራ አስቀምጦ ወደመንፈሳዊ አለም ያዘነበለዉ ሙሉቀን መለሰ በአንድ ወቅት ዘሪቱ ልትጠይቀዉ ቤቱ ድረስ መምጣቷን ተናግሮ ከዊትኒ ሂዉስተን ጋር አወዳድሮ ካደነቃት በሁዋላ ጸልዬላታለሁ ማለቱ ይታወሳል ። የዘሪቱ የዘፈን ሥራዎች የጥራት ደረጃቸዉ የላቀ ከመሆኑም በተጨማሪ ፣የሚያነሷቸዉ ሐሳቦችም ግዙፍና ያልተለመዱ የሚባሉ አይነት ናቸዉ ፣ አርቴፊሻል ፣ደግ አባቴ ፤ ክፉ ባሏ ፣ሚስትህ በጣም ፎንጋ ናት ፣ ለሚስቱ ካልሆነ ለማንም አይበጅም ፣ አዝማሪ ነኝ ና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል ። በተደጋጋሚ ሁለተኛ የዘፈን አልበሟ እያለቀ እንደነበረ ገልጻ የነበረችው ዘሪቱ ከበደ ፤ በአሁኑ ሰዓት የምትሰራቸዉ ሥራዎች መዝሙር ከመሆናቸዉ በተጨማሪ ፣በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ አምልኮ ስትመራ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ወጥተዋል ።

የስራ ዝርዝር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]