ዘ ሐበሻ ጋዜጣ
Jump to navigation
Jump to search
ዘ ሐበሻ ጋዜጣ በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ በጋዜጠኛ ሄኖክ ዓለማየሁ አሳታሚነት የሚታተምና የሚዘጋጅ ነጻ የግል ጋዜጣ ነው። ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት የማዶና ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ፤ እንዲሁም የመዲና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና አሳታሚ ነበር። ጋዜጠኛው በሃገሪቱ በሰፈነው የነጻ ፕሬስ ረገጣ በአንካሳ ሕጎች በተለያዩ ጊዜያት ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን በተለይ ያልተዘጉ ከ12 በላይ ክሶች በፍርድ ቤት እንጥልጥል ላይ እንዳለ በሱዳን በኩል አድርጎ ሃገሩን ጥሎ ለመሰደድ ከበቃ በኋላ በሊቢያ፣ በቱርክ የስደት ሕይወትን አሳልፎ በአሁኑ ወቅት በሚኒሶታ ይህንን ዘ-ሐበሻ የተባለውን ጋዜጣ በማሳተምና በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ከተመሰረተ ሁለተኛ ዓመቱን አሳልፏል።
ድረ ገጽ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |