ዝውውር ትንታኔ

ከውክፔዲያ
የዝውውር ውይይት መንገዶች

ዝውውር ትንታኔ (Transactional Analysis) ማለት በዘመናዊ ስነልቦና የሚጠቅም የችግር መፍትሄ ዘዴ ነው።

በዚህ መላ ምት የእያንዳንዱ ግለሠብ ባሕርይ በሦስት ደረጆች እነርሱም «አዋቂ»፣ «ወላጅ»፣ «ልጅ» ይከፋፈላል።

ሁለት ሰዎች ሲወያዩ፣ እያንዳንዱ ከሦስቱ ባህርዮች በአንድ ውስጥ አለ። ከዚህ የተነሣ እነዚህ ኹኔታዎች ይኖራሉ፦

  • አዋቂ ለ አዋቂ መወያየት
  • ወላጅ ለልጅ መወያየት
  • ልጅ ለወላጅ መወያየት

...ወዘተርፈ የሚሉ አይነት ምድቦች አሉ።

በተጨማሪ በመጽሐፉ «I'm OK, You're OK» («እኔ ደህና ነኝ፣ አንቱም ደህና ነህ») እንደ ተገለጠ፣ የሚከተሉ ኹኔቶች ሊኖሩ ይችላሉ፦

  • እኔ ደህና ነኝ፣ አንተም ደህና ነህ - ከሁሉ የሚሻ ለሥነልቦናም ጤናማ መወያየት፤
  • እኔ ደህና ነኝ፣ አንተ ግን መጥፎ ነህ - በዚህ ርዮት ብልጫ ይደረጋል፣ ጤናማ አይደለም
  • እኔ መጥፎ ነኝ፣ አንተ ደህና ነህ - ይህ ሰው ከሌሎች ችግር ይቀበላል
  • እኔ መጥፎ ነኝ፣ አንተም መጥፎ ነህ - ይህ ከሁሉ የባሰ ኹኔታ ሲሆን የሥነ ልቡና ዝቤት ያመልክታል።

ከታችኛው ወደ ላይኛው ኹኔታ ለመድረስ በ«ዝውውር ትንታኔ» ዘዴዎች ወይም በገቢር ማዳመጥአንጸባራቂ ማዳመጥ ወሳኙ ኢላማ ነው።

በዚያው መጽሐፍ ዝውውር ትንታኔ «ችግር እናገኛለን» ብሎ ስለማያስብ፣ በፍሮይድ መላምት ለተመሠረተ ስነልቦና ዘዴዎች ተቃራኒ ተብሏል።

የዝውውር ምሳሌዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እነዚህ ምሳሌዎች ከሥነ ጽሑፉ በመተርጐም ተወስደዋል።

ተስማሚ ዝውውሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በተስማሚ ዝውውሮች፣ ሁለቱ ተናጋሪዎች በአንድ ደረጃ ላይ አብረው ናቸው፣ ወይም በሚመላለሱ ደረጆች ናቸው፤ ያልተጠበቀ ሁናቴ አይሆንም።

  • ምሳሌ ፩፦
    • መጣጥፉን ለመጻፈ ችለሃል? (አዋቂ-አዋቂ)
    • አዎ፣ በኢሜል ልልክልህ ነው። (አዋቂ-አዋቂ)
  • ምሳሌ ፪፦
    • ከዚህ ስብስባ በኋላ ሂደን ሲኒማ ቤት ፊልምን እንይ? (ልጅ-ልጅ)
    • እወዳለሁ፣ ከሥራ ደክሞኛል፣ ምኑን እንይ? (ልጅ-ልጅ)
  • ምሳሌ ፫፦
    • ክፍልህን ማጽዳትህን መጨረስ ነበረብህ! (ወላጅ-ልጅ)
    • ጉዳዬን ተው፣ አደርጋለሁ! (ልጅ-ወላጅ)

ተሻጋሪ ዝውውሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተሻጋሪ ዝውውር አንዱ ተናጋሪ በማይመላለሰው ወይም በማይስማማው ሞድ ሲመልስ ነው፦

  • ምሳሌ ፩
    • መጣጥፉን ለመጻፍ ችለሃል? (አዋቂ-አዋቂ)
    • ጉዳዬን ተው፣ አደርጋለሁ! (ልጅ-ወላጅ)

ይህ አይነት ተሻጋሪ ዝውውር የመነጋገር እንቅፋት ይፈጥራል።

  • ምሳለ ፪፦
    • ክፍልህን ማጽዳትህን መጨረስ ነበረብህ! (ወላጅ-ልጅ)
    • እነሆ፣ አሁን እያደረግሁት ነው! (አዋቂ-አዋቂ)

ይህ አይነት ተሻጋሪ ዝውውር የተናጋሪዎች ሚዛን ሊቀይር ይሞክራል።