የሐዋርያት ሥራ ፮

ከውክፔዲያ
የሐዋርያት ሥራ ፮
ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ።
ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ።
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ቅዱስ ሉቃስ
የመጽሐፍ ዐርስት የሐዋርያት ሥራ
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፭ኛው መጽሐፍ
መደብ የቤተክርስቲያን ታሪክ


የሐዋርያት ሥራ ፮ በአዲስ ኪዳን ፭ኛ መጽሐፍ "የሐዋርያት ሥራ" ውስጥ የሚገኝ ሲሆን "ስድስተኛው ምዕራፍ" ነው ። የሚያተኩረውም በቀዳሚ ሰማዕት ቅዲስ እስጢፋኖስ የመንፈሳዊ ተጋድሎ ሥራዎች ላይ ነው ። ይህም በ፲፭ ንዑስ ክፍሎች ይካተታል ።

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፮

ቁጥር ፩ - ፲፭[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤በዚህም፡ወራት፡ደቀ፡መዛሙርት፡እየበዙ፡ሲኼዱ፡ከግሪክ፡አገር፡መጥተው፡የነበሩት፡አይሁድ፡በይሁዳ፡ ኖረው፡በነበሩት፡አይሁድ፡አንጐራጐሩባቸው፥በየቀኑ፡በተሠራው፡አገልግሎት፡መበለቶቻቸውን፡ችላ፡ ይሉባቸው፡ነበርና። 2፤ዐሥራ፡ኹለቱም፡ደቀ፡መዛሙርት፡ዅሉን፡ጠርተው፡እንዲህ፡አሏቸው፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ትተን፡ ማእዱን፡እናገለግል፡ዘንድ፡የሚገ፟ባ፟፡ነገር፡አይደለም። 3፤ወንድሞች፡ሆይ፥በመልካም፡የተመሰከረላቸውን፡መንፈስ፡ቅዱስና፡ጥበብም፡የሞላባቸውን፡ሰባት፡ሰዎች፡ ከእናንተ፡ምረጡ፥ለዚህም፡ጕዳይ፡እንሾማቸዋለን፤ 4፤እኛ፡ግን፡ለጸሎትና፡ቃሉን፡ለማገልገል፡እንተጋለን። 5፤ይህም፡ቃል፡ሕዝብን፡ዅሉ፡ደስ፡አሠኛቸው፤እምነትና፡መንፈስ፡ቅዱስም፡የሞላበትን፡ሰው፡ እስጢፋኖስን፡ፊልጶስንም፡ጵሮኮሮስንም፡ኒቃሮናንም፡ጢሞናንም፡ጳርሜናንም፡ወደ፡ይሁዲነት፡ገብቶ፡የነበረውን፡ የአንጾኪያውን፡ኒቆላዎስንም፡መረጡ። 6፤በሐዋርያትም፡ፊት፡አቆሟቸው፥ከጸለዩም፡በዃላ፡እጃቸውን፡ጫኑባቸው። 7፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡እየሰፋ፡ኼደ፥በኢየሩሳሌምም፡የደቀ፡መዛሙርት፡ቍጥር፡እጅግ፡እየበዛ፡ ኼደ፤ከካህናትም፡ብዙ፡ሰዎች፡ለሃይማኖት፡የታዘዙ፡ኾኑ። 8፤እስጢፋኖስም፡ጸጋንና፡ኀይልን፡ተሞልቶ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ድንቅንና፡ታላቅ፡ምልክትን፡ያደርግ፡ነበር። 9፤የነጻ፡ወጪዎች፡ከተባለችው፡ምኵራብም፡ከቀሬናና፡ከእስክንድርያም፡ሰዎች፡ከኪልቅያና፡ከእስያም፡ ከነበሩት፡አንዳንዶቹ፡ተነሥተው፡እስጢፋኖስን፡ይከራከሩት፡ነበር፤ 10፤ይናገርበት፡የነበረውንም፡ጥበብና፡መንፈስ፡ይቃወሙ፡ዘንድ፡አልቻሉም። 11፤በዚያን፡ጊዜ፦በሙሴ፡ላይ፡በእግዚአብሔርም፡ላይ፡የስድብን፡ነገር፡ሲናገር፡ሰምተነዋል፡የሚሉ፡ሰዎችን፡ አስነሡ። 12፤ሕዝቡንና፡ሽማግሌዎችንም፡ጻፊዎችንም፡አናደዱ፥ቀርበውም፡ያዙት፡ወደ፡ሸንጎም፡አመጡትና፦ 13፤ይህ፡ሰው፡በዚህ፡በተቀደሰው፡ስፍራ፡በሕግም፡ላይ፡የስድብን፡ነገር፡ለመናገር፡አይተውም፤ 14፤ይህ፡የናዝሬቱ፡ኢየሱስ፡ይህን፡ስፍራ፡ያፈርሰዋል፡ሙሴም፡ያስተላለፈልንን፡ሥርዐት፡ይለውጣል፡ሲል፡ ሰምተነዋልና፥የሚሉ፡የሐሰት፡ምስክሮችን፡አቆሙ። 15፤በሸንጎም፡የተቀመጡት፡ዅሉ፡ትኵር፡ብለው፡ሲመለከቱት፡እንደ፡መልአክ፡ፊት፡ኾኖ፡ፊቱን፡አዩት።