የመስቀል ጦርነቶች

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
የመስቀለኞች ክርስትያን ግዛቶች በ1127 ዓም

የመስቀል ጦርነቶች (ዛሬ እንደሚባሉ) በመካከለኛ ዘመን ምድረ እስራኤልን («ቅድስት አገር») ከእስልምና ሃይላት ለመያዝ ከ1087 እስከ 1283 ዓም ድረስ የሮሜ ፓፓዎች ያዋጁት ተከታታይ ሃይማኖታዊ ጦርነቶች ነበሩ።

ከመጀመርያው ጦርነት በኋላ፣ ክርስቲያን መስቀለኞቹ አንጾኪያን፣ ኢየሩሳሌምንና ሌሎች ሀገራት ከሰልጁክ ቱርክ ግዛት ወይም ከግብጽ አረቦች ለጊዜው ይዘው ነበር። ከመስቀለኞቹ ብዙዎቹ ከአሁኑ ፈረንሳይ ወይም ጀርመን - የፍራንኮች አገራት - ስለ ነበሩ፣ በቢዛንታይን ዘንድ «ፍራንኮይ፣ ፍራንጎይ»፣ በቱርኮችም ዘንድ «ፈረንጊ»፣ በአረብኛም «ፈረንጅ» ይባሉ ነበር፤ እንዲሁም ነጮች እስካሁን በአማርኛ «ፈረንጅ» በቻይንኛም «ፉላንግጂ» መባላቸው ከዚሁ ነው።

ከምዕራብ አውሮፓ በ1087 ዓም በፓፓ ኡርባን ትእዛዝ በወጡበት ሰዓት ኢየሩሳሌም በሰልጁኮች እጅ ስር ነበረች። «መስቀለኞቹ»ም በመንገዳቸው ላይ እያሉ ብዙ አይሁዶችን በእልቂት አስጨረሱ። እንዲሁም በግሪክ ኦርቶዶክስ ላይ ወንጀሎችን ይሠሩ ነበር። ሰልጁኮችን ሲታገሉ ለሙሐመድ (ቱርክኛ፦ መሐመት) ሲጮሁ እንደ አምላክ ወይም ጣኦት ስም ቆጥረውት ስሙን በፈረንሳይኛ «ማሖመት»፣ በሮማይስጥም ወደ «ባፎመት» ቀየሩት። ከዚያ አንዳንዶቹ በክኅደት የዲያቦሎስ ወይም 'ባፎመት' ተከታዮች ሆነው ብዙ አዲስ ክፉ አፈ ታሪክ ሠሩ። ኢየሩሳሌም በደረሱበት ወቅት ግብጻውያን ይዘውት ነበር። ፈረንጆቹ ግን በኢየሩሳሌም የተገኙትን እያንዳንዱን ወንድ፣ ሴትና ልጅ በሠይፍና በእሳት አስጨረሱ። ሰዶማዊ ሻለቃ ፩ ባልድዊን «የኢየኡሳሌም ንጉሥ» ተብሎ የፈረንጆች የኢየሩሳሌም መንግሥት ገዛ።