Jump to content

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፰

ከውክፔዲያ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፰

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፻፵፭ ፤ መኳንንት ደጆቻችሁን ክፈቱ ።
፻፵፮ ፤ የቆማቹህ ሰዎች ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ ።
፻፵፯ ፤ አቤቱ ሁሉን ለፈጠርህ ለማትታይ አምላክ ለአንተ ሰውነታችንን እንዘረጋለን ሁሉን ለምታዋርድ ለአንተ ራሳችንን እናዋርዳለን ሁሉን ለምታሰግድ ለአንተ እንሰግዳለን ሁሉን ለምትገዛ ለአንተ እንገዛለን ።
፻፵፰ ፤ የተሠወረውን የምትገልጽ የተገለጸውን ሁሉ የምትሠውር ሆይ በውስጥ ያለውን የምታወጣ በውጭ ያለውን የምታስገባ ሆይ ።
አሁንም በእውነት የሚጠሩህን የወገኖችህን ጩኸታቸውን ስማ ።
፻፵፱ ፤ በፍርሃት ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ስገዱ አቤቱ በፊትህ እንሰግዳለን እናመሰግንሃለንም ።
፻፶ ፤ ጸሎተ ንስሐ ።
፻፶፩ ፤ ተመልከት
ቅድሳት ለቅዱሳን ነው ። ቅዱስ አብ አንድ ነው ። ቅዱስ ወልድም አንድ ነው ። መንፈስ ቅዱስም አንድ ነው ።
፻፶፪ ፤ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋራ ይሁን ።
ከመንፈስ ጋራ ።
አቤቱ ክርስቶስ ማረን (፳፩ ጊዜ) ።
፻፶፫ ፤ በንስሐ ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ ።
፻፶፬ ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሕዝቡ ተመልሶ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ቅዳሴ ሐዋርያት ቁጥር ፺፭ - ፻፳፮ ።
፻፶፭ ፤ ሐዳፌ ነፍስ ። እናንተ የክርስቲያን ወገን ሆይ በዚች ቀን እንደተሰበሰባችሁ እንደዚሁ ክብርት በምትሆን በደብረፅዮንና በሰማይ ባለች ነፃ በምታወጣ በእየሩሳሌም ይሰብስባችሁ ።
፻፶፮ ፤ ይህንንም የማርያም የምስጋናዋን ቃል እንደሰማችሁ የሕፃናትን የምስጋና ቃል ይልቁንም ከጣዕሙ ብዛት የተነሳ አጥንትን የሚያለመልም የመላዕክትን ምስጋና እንደዚሁ ያሰማችሁ ።
፻፶፯ ፤ የእሳት ነበልባል ድንኳኖች ወደ ተተከሉበት የካህናት አለቃ ወዳለበት ያግባችሁ የተሳለ የፊቱ መልክ ከዚያ አለ ። ንጹሕ አክሊልና ብሩህ ልብስ ከዚያ አለ ። እርሱም ከላይ የተገኘ ነው እንጂ የስው እጅ ያልተጠበበበት ነው ።
፻፶፰ ፤ የቅዱሳን ማኀበር ወዳለበት ያግባችሁ ያስተማሩ የሐዋርያትም ማኀበር ድል የነሱ የሰማዕታት ማኀበር ብሩካን የሚሆኑ የጻድቃንም ማኀበር የተሾሙ የካህናት ማኀበር ትጉሃን የሚሆኑ የመላዕክት ማኀበር ፍፁማን ደናግልና የመነኮሳት ማኀበር ወዳለበት ያግባችሁ ። ከሁሉ በላይ ከሆነች ከአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍፁም አንድነቷ ሁሉ ጋራ ከነርሱም ጋራ ታቦትዘዶር ወዳለችበት ይህችውም እመቤታችን ማርያም ናት ።
፻፶፱ ፤ እንግዲህ ሞትን የምታለብስና ወደ ሲኦል የምታወርድ ትዕቢትና መታጀርንም ጌጥ አናድርግ ።
፻፷ ፤ እንግዲህ የሥጋ ንጽሕና ብቻ ያይደለ ትሕትናን ከንጽሕና ጋራ ገንዘብ እናድርግ ። መንፈስን ንጹሕ በማድረግ ነብያት እግዚአብሔርን አይተውታልና ።
፻፷፩ ፤ እንግዲህ እንደሐዋርያት ፍቅርን የዋሃትንም ገንዘብ እናድርግ ጌታቸውን ወደውታልና የዓመፃ ማሠሪያን ሁሉ ያሥሩ ይፈቱም ዘንድ እንደርሱ ያለውን ሥልጣን የሰጣቸው ።