Jump to content

የሩዝ ቅቅል

ከውክፔዲያ

የሩዝ ቅቅል) ለ3 ሰው

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ሩዝ 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ

አዘገጃጀት 1. ሩዙን በደንብ አጥቦ ደረቅ እስኪል ማንጠፍጠፍ፤ 2. ዘይት በደረቅ ብረት ድስት ውስጥ አሙቆ ቀይ ሸንኩርቱን በመጨመር ማቁላላት፤ 3. ሩዙን በላዩ ጨምሮ ደርቆ ቀላ ያለ መልክ እስኪያወጣ ማቁላላት፤ 4. ሩዙ በተለካበት ዕቃ እጥፍ የሚሆን ውሃ መጨመር፤ 5. አንዴ ብቻ አማስሎ እስኪበስል መተው፤ 6. ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ ማስተካከል፤ 7. ውሃው መጦ ሲበስል ማውጣት፤ 8. ውሃው መጦ ሩዙ ካልበሰለ በማንኪያ መሃሉ ላይ ወጋ አድርጎ የፈላ ውሃ በመጨመር እንደገና እስኪመጥ መጠበቅና ለገበታ ሲፈለግ ከሶሱ ጋር ደባልቆ ወይም ለየብቻ ማቅረብ፡፡