የሸዋ ኣረም

ከውክፔዲያ
የሸዋ አረም

የሸዋ ኣረም (Galinsoga parviflora) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሸዋ አረም እስከ 75 ሴንቲ ሜትር ድረስ ሊሆን ይችላል። ባለ ቅርንጫፍ እጽ፣ ፊት ለፊት የሆኑ ባለ አገዳ ቅጠሎቹ ዳርቻቸው ጥርስ ባለ ሚስማር ላይ ነው። አበቦቹ በትንንሽ ራሶች ናቸው፣ ራሱም በ3-8 ነጭ አበቢቶች ተከብቦ፣ እነዚህም አበቢቶች 1 mm ሆነው ሦስት ግርብ ያላቸው ናቸው። በመሃሉ ያሉት አበቢቶች ቢጫ ሲሆኑ ቱቦአዊ ቅርጽ አላቸው።[1][2]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ስሙ «የሸዋ» ቢባልም እንዲያውም መነሻው በፔሩ ነበረ። አሁን ወደ ብዙ አህጉራት ተስፋፍቶ በአጠቃላይ እንደ አረም ይቆጠራል።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኮሎምቢያ አገር አበሳሰል «አሕያኮ» በሚባል ሾርባ አይነት ውስጥ እንደ ቅመም ይበላል። በሠላጣ ደግሞ ሊበላ ይችላል።

በኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት፣ የትኩስ ቅጠልና ህብራበባ ውጥ የቆዳ ቁስል ለማከም ይጠቀማል።[3]


  1. ^ Clapham, A.R., Tutin, T.G. and Warburg, E.F. 1968 Excursion Flora of the British Isles. Cambridge University Press. መለጠፊያ:ISBN
  2. ^ "Flora of China, Galinsoga parviflora Cavanilles, 1795.". Archived from the original on 2020-07-27. በ2017-07-10 የተወሰደ.
  3. ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.