የሻባካ ድንጋይ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
የሻባኮ ድንጋይ ከነወፍጮው ጉዳት

የሻባካ ድንጋይግብጽ አዲስ መንግሥት (ምሥር) 25ኛ ሥርወ መንግሥት (ከ700 ዓክልበ. ገደማ) የደረሰ ቅርስ ነው። በዚህ ታላቅ ድንጋይ የተቀረጸው የሃይሮግሊፍ ጽሑፍ በኩሻዊው ንጉሥ ሻባካ ትዕዛዝ ትል ከበላ ከጥንታዊ ብራና እንደ ተቀዳ ይላል። ሻባካ የብራናውን ወረቀት በአንድ የሜምፎስ ቤተ መቅደስ አገኝቶት ቃሉ እንዳይጠፋ እንዲቀረጽ አዘዘ ይላል። ሆኖም በኋለኛ ዘመን ድንጋዩ እንደ ወፍጮ ተጠቅሞ ብዙ ሃይሮግሊፍ ጠፋ፤ ከዚህ ጉዳት የተነሣ በሙሉ ማንበቡ አይቻልም።

ጽሑፉ በተለይ የጥንታዊ ግብጽ አፈ ታሪክ ይገልጻል። በጥንታዊ ግብጻውያን እምነት ሴት የተባለው ትንሽ ወንድሙን ዖሴሮስን (ቄንቲያሜንቱን) በታቸኛ አባይ ወንዝ (ስሜን ግብጽ) አሰጥሞ ከገደለው በኋላ፣ እሱ ደቡብ ግብጽ ተሸለመው። የዖሴሮስ በኲር ሔሩ እንዲሁም ስሜኑን ተቀበለ። ትንሽ ጊዜ አልፎ ግን ሔሩ የአማልክት ሞገስ አገኝቶ ሁለቱን አገሮች ያዘ። ከብዙ ትግል በኋላ ሁለቱ ወንድሞች ተስማሙና አብረው ፈርዖኖቹን ወለዱ።

ይህ አፈ ታሪክ ምናልባት ስለ ላይኛ ግብጽታችኛ ግብጽ ታሪካዊ ውሕደት በጣም የተዛበ ወሬ ይሆናል።