የሻንሺ ምድር መንቀጥቀጥ
Appearance
የሻንሺ ምድር መንቀጥቀጥ በጥር 15 ቀን 1548 ዓ.ም. በቻይና የደረሰባት ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ነበር። 830,000 ያሕል ሰዎች በመግደሉ ይህ ከታሪክ መዝገብ ሁሉ እስካሁን ድረስ አንደኛው ታላቅ መንቀጥቀጥ ነበር። ያንጊዜ ብዙ ሕዝብ በዋሻ ውስጥ ስለ ኖሩ በአወዳደቁ ወዲያው ጠፉ። ይህ የሆነበት ወቅት በሚንግ ሥርወ መንግስት በጅያጂንግ ንጉሥ ዘመን ነበር።
ዛሬ የመሬት ጥናት ሊቃውንት ታላቅነቱ በመጠን 8 እንደ ደረሰ ይገምታሉ። በቻይና ዜና መዋዕል (ታሪካዊ መዝገቦች) እንዲህ ተጽፎ ይገኛል፡-
- «በ1548 ዓ.ም. በጋ፣ የምድር መንቀጥቀጥ መቅሠፍት በሻንሺ እና ሻንሺ* አውራጆች ሆነ። በኛ ኋ ወረዳ ልዩ ልዩ መጥፎ ዕድል ደረሰ። ተራሮችና ወንዞች ተለዋወጡ መንገዶችም ጠፉ። በአንዳንድ ስፍራ መሬቱ ከድንገት ተነሥቶ አዲስ ኮረብታ ተፈጠረ፣ ወይም ብርግድ ብሎ አዲስ ሸለቆ ሆነ። በሌላ ዙሪያ ፈሳሽ ከመቅፅበት ፈለቀ፣ ወይም ምድር ተሰብራ አዲስ ጉድጓዶች ታዩ። ጎጆዎች፣ መሥሪያ በቶች፣ መቅደሶችና ቅጥሮች ሁሉ በድንገት ፈረሱ።»
- (* - በቻይና ሁለት ጎረቤት አውራጆች "ሻንሺ" ሲባሉ በድምጽ ጣዕመ ዜማ ግን ይለያያሉ፡፡)