የቆስጣና የዕንቁላል ጥብስ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

መጠን


ግማሽ ኪሎ ቆስጣ 2 ቲማቲም የተከተፈ 2 ራስ ቀይ ሽንኩርት የተከተፈ ዘይት 3 ዕንቁላል ጨው እንደ አስፈላጊነቱአሠራሩ 1. ቆስጣውን ሸምጥጦ አጥቦ ማብሰል፤ 2. ሽንኩርቱን በዘይት አቁላልቶ ቲማቲም መጨመር፤ 3. ትንሽ ካቁላሉ በኋላ ቆስጣውን ከውኃው አጠንፍፎና፤ ጨምቆ ሽንኩርቱ ውስጥ መጨመር፤ 4. ሲበስል ጨው ጨምሮ አስማምቶ ማውረድ፤ 5. ቀዝቀዝ ሲል እንቁላሉን መትቶ ጎመኑ ላይ መጨመርና ማዋሀድ፤ 6. በመጥበሻ ዘይት አሙቆ እያገላበጡ እንደቂጣ መጋገር በላይም በታቹም ቡኒ ሲመስል (ቀላ ሲል) ማውጣት፤ 7. ከወረደ በኋላ 4 መአዘን 4 መአዘን እያደረጉ ቆርጦ ማቅረብ፡፡