Jump to content

የበረሃዋ ድመት

ከውክፔዲያ
ሳንድ ካት
የበረሀዋ ድመት

የምትገኝበት አካባቢ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሰሃራ በረሃ መካከለኛ አካባቢ፣ በዓረብ አገሮች በሙሉና በማዕከላዊ እስያ አንዳንድ ክፍሎች

ተባዕቱ ከ2 እስከ 3 ኪሎ ግራም

ርዝመት (ጅራትን አይጨምርም)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከ40 እስከ 57 ሴንቲ ሜትር

ከ20 እስከ 30 ሴንቲ ሜትር

ጆሯቸው ከሩቅ ስለሚሰማ የሚያድኑት እንስሳ ከመሬት በታች ቢሆንም እንኳ ሊያገኙት ይችላሉ። ተባዕቱ ድመት ተጓዳኝ ለማግኘት ቀጭን የሆነ ኃይለኛ ጩኸት ያሰማል። እንስቷም ይህንን ድምፅ ከረጅም ርቀት መስማት ትችላለች። መዳፎቻቸው በፀጉር የተሸፈኑ ናቸው፤ ይህም በሚሄዱበት ጊዜ አሸዋ ውስጥ እንዳይሰምጡ የሚረዳቸው ከመሆኑም ሌላ መዳፋቸውን ቅዝቃዜም ሆነ ሙቀት እንዳይጎዳው ይከላከልላቸዋል። የጆሮዎቻቸው ውስጠኛ ክፍል ጥቅጥቅ ባለ ነጭ ፀጉር የተሸፈነ መሆኑ ነፋስ በሚኖርበት ጊዜ አሸዋ ጆሯቸው ውስጥ እንዳይገባ ይከላከልላቸዋል። የእነዚህ ድመቶች መዳፍ ጥቅጥቅ ባለ ፀጉር የተሸፈነ በመሆኑ ዱካቸውን ተከታትሎ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። እነዚህ ድመቶች ከሚበሉት እንስሳ በሚያገኙት ውኃ ብቻ መኖር ይችላሉ። የካራኩም በረሃ አሸዋ እስከ 80 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ ሙቀት ሊኖረው ይችላል። በሌሎች ጊዜያት ደግሞ የሙቀቱ መጠን ከዜሮ በታች እስከ 25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊወርድ ይችላል።