Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

የበግ እግር አሮስቶ

ከውክፔዲያ

የበግ እግር አሮስቶ ለ7 ሰው አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች - 3 መካከለኛ የበግ እግር ከነአጥንቱ - 4 መካከለኛ ካሮት - 4 ዝንጣፊ ሲለሪ - 2 ቀጫጭን ባሮ ሽንኩርት - 5 መካከለኛ ቀይ ሽንኩርት - 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት - 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ቬጅቴብል ስቶክ (የአትክልት መረቅ) - 3 የሾርባ ማንኪያ የወይን ጠጅ - 3 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት - 1 የሻይ ማንኪያ ጨው - 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ - 5 ትላልቅ ፍሬ ነጭ ሽንኩርት

አዘገጃጀት

1. ሥጋውን ማጽዳት፤ 2. ካሮቱንና ቀይ ሽንኩርቱን በቁመቱ አራት ቦታ መቆራረጥ፤ 3. ሲለሪውንና ባሮ ሽንኩርቱን አጥቦ ስምንት ቦታ መቆራረጥ፤ 4. ሥጋውን በቢላዋ እየበሱ ከየዓይነቱ እያደባለቁ በሺሽ ክበብ ሽቦ በመታገዝ ሲለሪ፣ ቀይ ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርት፣ ካሮትና ባሮ ሽንኩርቱን ልጦ ሳይቆራርጡ መክተት፤ 5. በትልቅ ድስት ዘይት አግሎ ሥጋውን በመጨመር ወርቃማ መልክ እስኪያወጣ እያገላበጡ መጥበስ፤ 6. መረቁን አሙቆ ድስቱ ውስጥ ጨምሮ እንዲበስል መተው፤ 7. ሲበስል ስጋውን ማውጣት፤ 8. ከድስቱ ውስጥ ዘይቱን ማጥለልና መረቁን አንተክትኮ መጠኑ እንዲቀንስ ካደረጉ በኋላ ወይኑን ጨምሮ ግማሽ እስኪሆን ማንተክተክ፤ 9. ዱቄቱን ጨምሮ በደንብ ካሹ በኋላ ጨውና ቁንዶ በርበሬ መጨመር፤ 10. ስጋውን በስሱ ቆራርጦ ማባያውን በላዩ ማፍሰስ ወይም ለየብቻ ማቅረብ፤ 11. ከተጠበሰ ድንችና ከክብ ካሮት ወይም በቁመቱ ተቆርጦ ከተቀቀለ ካሮት ጋር ማቅረብ ይቻላል፡፡