የተልባ ማሻው ሚካኤል

ከውክፔዲያ

የተልባ ማሻው ሚካኤል

(36)አለቃ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲመለሱ ያው የግድ የአባይን በረሀ ማቋረጥ ነበረባቸው። አብረዋቸው የነበሩ መንገደኞች በቃ የአባይ ሽፍታ ሊዘርፈን ነው ብለው ሲያለቃቅሱ። አለቃ ብራችሁን ሰብስቡና አምጡ ብለው - መንገድ ሲሄዱ ተልባ እየወቀጡ የሚበሉበት ሙቀጫ ውስጥ ብሩን በሙሉ ይጨምሩና አፉን ወትፈው፤ ሙቀጫውን የቤተ ክርስቲያን ጨርቅ አልብሰው ለአንዱ መንገደኛ እንደታቦት አሽክመው ሲጓዙ ሽፍቶቹ ዘንድ ይደርሳሉ። ሽፍቶቹም ብቅ ብቅ ይሉና «ምንድናችሁ?» ይላሉ። አለቃም ፈጠን ብለው «ታቦት ልናስገባ ይዘን የምንመጣ መንገደኞች ነን» ይላሉ። አንዱ ሽፍታም «የታቦቱ ስም ማን ነው?» ይላል። አለቃም «የተልባ ማሻው ሚካኤል ነው» ብለው መለሱ። ሽፍቶቹም ተሳልመው መንገደኞቹም በሰላም በረሀውን አለፉ።