የተቃርኖ አራት ማዕዘን

ከውክፔዲያ
የተቃርኖ አራት ማዕዘን በስብስብ ቬን ዲያግራም እንደሚብራራ

የተቃርኖ አራት ማዕዘን በአራቱ የተቃራኒ አይነቶች መካከል ያለውን ዝምድና እና ልዩነት የሚያሳይ የሥነ አመክንዮ ዘዴ ነው። ሁሉም ተቃርኖዎች አንድ አይነት አይደሉም። ለምሳሌ፦

ረቂቅ ፩)  ሁሉም ሰው ኬኒያዊ ነው። 
ረቂቅ ፪)  ምንም ሰው ኬኒያዊ ነው።  
ረቂቅ ፫)  አንድ አንድ ሰዎች ኬኒያዊ አይደሉም።  
ረቂቅ ፬)  አንድ አንድ ሰዎች ኬኒያዊ ናቸው።  

ረቂቅ ፩ን የሚመስሉ ዓይነት ዓረፍተ ነገሮች ሁለንተናዊ አዎታ ይባላሉ፤ ረቂቅ ፪ ሁለንተናዊ አሉታ ይባላል፣ ረቂቅ ፫ ልዩ አሉታ ሲባል፣ ረቂቅ ፬ ልዩ አዎንታ ይባላል።

በረቂቅ ፩ እና ረቂቅ ፪ መካከል ያለው ተቃርኖ የተጻራሪ ዓይነት ይባላል። በ፩ እና ፫ መካከል ያለው ተቃርኖ የመጣረስ ዓይነት ሲሆን በ፩ እና ፬ መካከል ያለው ግንኙነት ደግሞ ንዑስ ተከታይ ሊባል ይቻላል። በ፫ እና ፬ መካከል ያለው ግንኙነት ንዑስ ተጻርኖ ይባላል። ቁጥር ፪ እና ቁጥር ፬ የመጣረስ ግንኙነት አላቸው።

ሁለት  ተጻራሪ ረቂቆች በአንድ ጊዜ ውሸት ሊሆኑ ይችላሉ፣  ግን በአንድ ጊዜ እውነት ሊሆኑ ከቶ አይችሉም። 
ሁለት የተጣረሱ ረቂቆች አንድ ላይ  ውሸት ሊሆኑ አይችሉም፣ እንዲሁ አንድ ላይ እውነት ሊሆኑ ፍጹም አይችሉም።
ሁለት ንዑስ ተጻርኖዎች  አንድ ላይ እውነት ሊሆኑ ይችላሉ፣  ነገር ግን በአንድ ላይ ውሸት ሊሆኑ አይችሉም። 
ሁለት ንዑስ ተከታዮች አንድ ላይ እውነት ሊሆኑ ይችላሉ፣ እንዲሁ አንድ ላይ ውሸት ሊሆኑ ይችላሉ።