Jump to content

የንግሥት ማክዳ የኢየሩሳሌም ጉዞ

ከውክፔዲያ

ክብር ይግባውና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት አንድ ሺህ ዓመት ገደማ የኢትዮጵያ ንግሥት የነበረችና በቅዱሳን መጻሕፍት ንግሥተ ሳባ/አዜብ ተብላ የምትታወቀው ታላቅ ሴት ነበረች። ይህቺውም ንግሥት ግዛቷን እስከ አረቢያ አስፋፍታ ሀገራችንን በኃይልና በሀብት ከፍ ያደረገች ስመ ገናና ንግሥት ነበረች። ንግሥት ማክዳ ከአባቶቿ በወረሰችው አምልኮተ እግዚአብሔር ስትኖር ሳለ የጠቢቡ ሶሎሞንን ዝና በባለሟሏ ታምሪን አማካኝነት ሰማች። በእምነት እርሷን የሚመስል በማግኘቷ በመደሰት፤ የሰማችውን ዓይታ ለማረጋገጥ መንፈሳዊ ቅናት ቀሰቀሳት በዚህም ምክንያት ወደ ምድረ እስራኤል ተጓዘች፡፡ በዚያም ጥበበኛውን ንጉሥ ሶሎሞንን ጥበቡን ለማወቅ በጥበብ ፈተነችው፤ ውጤቱም ከሰማችው በላይ መሆኑንና ስለተሰጠውም ጥበብ አድንቃ ለዚህ ክብር ያበቃውን የጸጋ ባለቤት እግዚአብሔርን ማመስገኗ በቅዱሳት መጻሕፍት ተነግሮላታል። መጽ ነገ ፲፣ ማቴ. ፲፪፥ ፵፪ ንግሥት ማክዳ በዚህ ጉዞዋ የንጉሥ ሰሎሞንን አምልኮና የአስተዳደር ጥበብ ቀስማ፣ እንዲሁም በፈቃደ እግዚአብሔር ከንጉሡ ቀዳማዊ ምኒልክን ፀንሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳለች። ልጆች ንጉሡ ለንግሥቲቱ ክብር ዴርሡልጣን ተብሎ የሚታወቀውን ቦታ ርስት አድርጎ ሰጥቷታል፤ ይህም እስከዛሬ ድረስ በሀገረ እስራኤል የኢትዮጵያ ርስትና ገዳም ሆኖ ይገኛል።