Jump to content

የአትክልት መረቅ

ከውክፔዲያ

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች - 8 የሾርባ ማንኪያ (200 ግራም) የገበታ ቅቤ - 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት - 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በስሱ የተቆረጠ ባሮ ሽንኩርት

- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ሴለሪ (የሾርባ ቅጠል) - 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ጥቅል ጐመን - 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተገረደፈ ቲማቲም - 2 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት - 1 የላውሮ ቅጠል - 12 ሊትር ቀዝቃዛ ውሃ - 1 የሾርባ ማንኪያ ጨው

አዘገጃጀት 1. በትልቅ ብረት ድስት ቅቤውን ማቅለጥ፤ 2. ቀይ ሽንኩርት፣ ባሮና ሴለሪውን ጨምሮ በነጩ ማቁላላት፤ 3. ጥቅል ጎመኑን፣ ቲማቲሙን፣ ነጭ ሽንኩርቱንና ላውሮውን ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤ 4. ውሃውንና ጨዉን ጨምሮ ለሰስ ባለ እሳት ላይ ለአንድ ሰዓት ማንተክተክ፤ 5. አውጥቶ ትንሽ ቀዝቀዝ ሲል በንጹሕ አቡጀዲ ማጥለል፤ 6. አቀዝቅዞ በተገቢው ዕቃ ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ፡፡

(ደብረ ወርቅ አባተ፤ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 1993)