የአጼ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

የአጼ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል በግዕዝ እንደተጻፈና በማኑኤል አልሜዳ ወደ ፖርቱጋልኛ እንደተተረጎመ ፣ በ1888 በሊዝቦን ፖርቱጋል እንደታተመ ከታች በስተግራ ቀርቧል። ዜና መዋዕሉ የአጼፋሲለደስ አባት የነበሩትን የአጼሱሰንዮስን ዘመን የመዘገበ ሰነድ ነው። አጼ ሱሰንዮስ፣ ምንም እንኳ በብዙ መልኩ የተሳካ አመራር፣ በተለይ በጦርነት፣ ላይ ቢያሳዩም፣ በኋላ ግን ከፖርቱጋሎች ጋር በነበራቸው ቀረቤታ ሃይማኖታቸውን ወደ ካቶሊክ መቀየራቸው እንዲሁም ከውጭ ያስመጡት የካቶሊክ ጳጳስ አልፎንሶ ሜንዴዝ ባሳየው ግትርነትና ጨካኝነት ብዙ አመጽ ተነስቶባቸው በመጨረሻ ዘመናቸው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለልጃቸው ፋሲለደስ አስረክበው ያለፉ ሰው ነበሩ። ከታች በስተቀኝ በኩል የሱሰንዮስን ዜና መዋዕል በተሟላ መልኩ የሚተችና የሚተነትን ጽሑፍ በፖርቱጋልኛ ቀርቧል።

  • ይህ በኢትዮጵያዊ አይን እማኝ የተመዘገበው ዜና መዋዕል በግዕዝ ስለሆነ ለማንበብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ግዕዝ ወይም ፖርቱጋልኛ በትክክል የሚያውቅ ሰው ወደ አማርኛ ቢተርጉመው ለአንባቢ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [1] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች በግዕዝና በፖርቱጊዝ ማንበብ ይችላላሉ
የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [2] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች በፖርቱጊዝ የቀረበውን ሙሉ ትንታኔ ማንበብ ይችላላሉ