Jump to content

የኢትዮጵያ መጓጓዣ

ከውክፔዲያ

ኢትዮጵያ ጅማሮው ከማይታወቅበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ለረጅም አመታት የጋማ ከብቶች እንደ ዋና መጓጓዣነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። በአሁኑ ሰዓት በሰለጠኑት የሃገሪቱ ከተሞች የአየር ፣ የየብስ (ባቡር ፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች) ብሎም የውሃ ላይ መጓጓዣዎች (አነስተኛ መርከቦች ፣ ጀልባዎች ፣ ታንኳዎች) በጥቅም ላይ ውለው የሚታዩ ቢሆንም አሁንም በሃገሪቱ አብዛኛው ክፍል የጋማ ከብቶች በዋናነት ለመጓጓዣነት ብሎም ለጭነት አገልግሎትነት በመዋል ላይ ይገኛሉ።