Jump to content

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት

ከውክፔዲያ

የንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ነው። የኢፌዴሪ መንግስት ንብረት የሆነው። ከ 5 ዓመታት የጉልበት ሥራ በኋላ በየካቲት 5, 2014 ተመርቋል። ሕንፃው በአዲስ አበባ እና በመላ አገሪቱ ውስጥ ረጅሙ ነው። በአፍሪካ 3ኛው እና በአለም 1450ኛ ረጅሙ። ባንኩ 303 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ15 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል ሕንፃው 209.3 ሜትር ቁመት ወይም ወደ 687 ጫማ ነው። [1][2][3][4][5]


ህንጻው 165,000 ስኩዌር ጫማ መሬት ላይ ነው።"209.15 ሜትር ርዝመት ያለው (ቁመት) ተብሎ የተገለፀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋናውን ፋሲሊቲ ግንባታ ለማጠናቀቅ አምስት አመት ከ11 ወር እንደፈጀም ተነግሯል።"[6][7][8] 11 እና 13 ፎቅ ከፍታ ያላቸው ከንግድ ባንክ ህንፃዎች ውጪ ሌሎች ሕንፃዎችም አሉ።እነዚህ ሕንፃዎች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ሕንፃ ጋር የተገናኙ ናቸው።የተቀሩት የባንኩ ሁለት ክፍሎች ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ህንጻ ተጨማሪ ቦታ ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን ተያያዥነት ያላቸው እና በቀላሉ በሰዎች የሚተላለፉ እና የሚሄዱ ናቸው። "የካቲት 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) 80 ወርቃማ ዓመታትን ያስቆጠረው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባው አዲስ ህንጻ በዛሬው እለት ይመረቃል። በኢትዮጵያ 117 ዓመታትን ያልበለጠ እድሜ ባስቆጠረው የባንክ ስራ ታሪክ ትልቅ አሻራ ይዞ የዘለቀ የፋይናንስ ተቋም ነው፤የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ። በ1935 ዓ.ም በ1 ሚሊዮን የማሪያትሬዛ መነሻ ካፒታል ‘የኢትዮጵያ መንግስት ባንክ’ በሚል የብሔራዊ ባንክን እና የንግድ ባንክን ሚና አጣምሮ በመያዝ ነበር የተመሰረተው። በ1955 ዓ.ም ብሔራዊ ባንክ ሲቋቋም ‘የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ’ በሚል ስያሜ የአገሪቷን ገንዘብ ተቆጣጣሪነት ሚናውን በመተው በንግድ ሥራ ዘርፉን ይዞ ቀጠለ። 80 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ አንጋፋ ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ ከ1 ሺህ 800 በላይ ቅርንጫፎች እና ከ34 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አፍርቷል። 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር ግን በአገሪቱ ብቻ ሳይሆን በቀጣናው ሰማይ ታካኪ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ገንብቶ በዛሬው እለት ያስመርቃል።"[9][10][11][12]





  1. ^ https://www.lekreports.com/ethiopia-inaugurates-303-million-dollar-bank-headquarters-building/
  2. ^ https://www.skyscrapercenter.com/building/commercial-bank-of-ethiopia/8825
  3. ^ https://www.fanabc.com/የኢትዮጵያ-ንግድ-ባንክ-ለዓለም-አቀፍ-ውድ/
  4. ^ https://www.ethioexplorer.com/80ኛ-ዓመቱን-የሚያከብረው-የኢትዮጵያ-ንግድ/
  5. ^ https://ethiopiainsider.com/2022/5867/
  6. ^ https://www.ethiopianreporter.com/article/24695
  7. ^ https://addismayor.gov.et/am/ሀቆች-ስለ-ግዝፉ-የኢትዮጵያ-ንግድ-ባንክ-ዋ/
  8. ^ https://am.constructionreviewonline.com/news/ethiopia/ethiopia-industrial-inputs-development-enterprise-headquarters-building-design-complete/
  9. ^ https://amharic.zehabesha.com/archives/127146
  10. ^ https://am.al-ain.com/article/ethiopia-will-open-its-doors-to-international-banks-pm-abiy-ahemed
  11. ^ https://waltainfo.com/am/ጠ-ሚ-ር-ዐቢይ-የኢትዮጵያ-ንግድ-ባንክ-ህንጻ/
  12. ^ https://www.ena.et/?p=161729