የእብድ ውሻ በሽታ

ከውክፔዲያ
Rabies
Classification and external resources

የእብድ ወሻ በሽታ ያለበት ውሻ ሰውነቱ በተሽመደመደበት (ድህረ-እብደት) ደረጃ
ICD-10 A82
DiseasesDB 11148
MedlinePlus 001334
eMedicine med/1374 መለጠፊያ:EMedicine2 መለጠፊያ:EMedicine2
Patient UK የእብድ ውሻ በሽታ
MeSH D011818


የእብድ ውሻ በሽታየቫይረስ በሽታ ሆኖ ከፍተኛ የየአንጎል መጉረብረብን በሰዎች እና በሌሎች ደመ-ሞቃት እንስሳት ላይ የሚያስከትል ነው።[1] ቅድሚያ ምልክቶቹ ትኩሳት እና በተነከሱበት ቦታ ማሳከክ/ማቃጠልን ያካትታል።[1] እነዚህ ምልክቶች ከሚከተሉት አንድ ወይም የበለጡ ምልክቶች አስከትለው ይመጣሉ:- ሃይል የታከለባቸው የሰውነት እንቅስቃሴዎች፣ ከቁጥጥር ወጭ የሆ መሸበር፣ የውሀ ፍራቻ, የሰውነት ክፍለን ለማንቀሳቀስ አለመቻል፣ ግራ መጋባት፣ እና ህሊናን መሳት[1] ምልክቶቹ ከታዩ በኋላ፣ የእብድ ውሻ በሽታ በአብላጫው ሁልጊዜ ሞትን ያስከትላል። [1] በበሽታው በመያዘዎ እና ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩበት የጊዜ ገደብ በአብዛኛውን ጊዜ ከአንድ እሰከ ሶስት ወራት ባሉት ጊዜ ውስጥ ነው። ሆኖም ግን፣ ይህ የጊዜ ገደብ ከሳምንት ባነሰ እና ከአመት በበለጠ ጊዜ ሊለያይ ይችላል። [1] የጊዜ ገደቡ የሚወስነው የበሽታ አምጭው ረቂቅ ህዋስ ወደ የማዕከላዊ የነርብ ስርዓትለመድረስ በሚፈጅበት እርቀት ነው።[2]

የእብድ ውሻ በሽታ ወደ ሰዎች የሚተላለፈው በሌሎች እንስሳት ነው። በበሽታው የተበከለ እንስሳ ሌላ እንስሳ ወይም ሰው ሲቧጭር ወይም ሲናከስ የእብድ ወሻ በሽታ ሊተላለፍ ይችላል። [1] የተበከለ እንስሳ ምራቅ ከሌላ እንስሳ ወይም ሰው የሰውነት ፈሳሽ አመንጭ ህዋስ ያሉበት ማስተላለፊያ ጋር ከተነካካ የእብድ ወሻ በሽታ ሊተላለፍ ይችላል።[1] አብዛኛዎቹ በሰዎች ላይ የተከሰት የእብድ ወሻ በሽታዎች መንስሄዎች የውሻ ንክሻ ናቸው።[1] በአብዛኛው ውሾች የእብድ ውሻ በሽታ ባለባቸው ሀገራት ከ99% በላይ የእብድ ውሻ በሽታ ክስተቶች መንስኤዎች የውሻ ንክሻዎች ናቸው። [3]አሜሪካዎች ውስጥ፣ የሌሊት ወፎች በአብላጫ የተለመደ የእብድ ውሻ በሽታ መንስኤ ናቸው፣ እናም ሰዎች ላይ ከ5% በታች የእብድ ውሻ በሽታ ክስተቶች መንስኤ ውሾች ናቸው።[1][3] ረጃጅም የፊት ጥርስ ያላቸው ትንንሽ አጥቢ እንስሳት/አይጥ/ሽኮኮ/.. በእበድ ወሻ በሽታ የመያዝ እድላቸው በጣም ኢሚንት ነው። [3] የእብድ ወሻ በሽታ ረቂቅ ህዋስ ወደ አንጎል የሚጓዘው ፐርፈሪያል ነርብስበመከተል ነው። በሽታው ሊታወቅ የሚችለው ምልክቶቹ ከጀመሩ በኋላ ነው። [1]

የተወሰነ ቁጥር ባለቸው የአለም ከፍሎች የእንስሳ ቁጥጥር እና ክትባት መርሀግብሮች በውሻ የሚመጣ የእብድ ውሻ በሽታዎችን ተጋላጭነት ቀንሰዋል። [1] ከፍተኛ ተጋለጭነት ላለባቸው ሰዎች ለበሽታው ከመጋለጣቸው በፊት አስቀድሞ የመከላከያ ክትባትን መስጠት ይመከራል። ከፍተኛ-ተጋላጭ ቡድን ከሌሊት ወፎች ጋር የሚሰሩ ወይም ለረዥም ጊዜያት የእብድ ወሻ በሽታ በአብዛኛው የሚከሰትበት ቦታ የሚሰሩትን ሰዎች ያካትታል። [1] ለእብድ ወሻ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች፣ የእብድ ውሻ በሽታ ክትባት እና አንዳንድ ጊዜም የእብድ ወሻ በሽታ ኢሚዩኖግሎቢን ታካሚው የእብድ ውሻ በሽታ ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት ህክምናውን ከአገኘ በሽታውን ለመከላከል ወጤታማ ነው። [1] የተነከሰውን እና የተቧጨረውን ቦታ ለ15 ደቂቃ በውሃ እና በሳሙና ማጠብ፣ ፕሮቪዳን አዮዲን, ወይም የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሾች ቫይረሱን ሊገሉት ስለሚችሉ እና እንዲሁም የእብድ ወሻ በሽታን መተላለፍን ለመከላለከል በተወሰነ መልኩ ወጤታማ ናቸው።[1] ጥቂት ሰዎች ብቻ የእብድ ወሻ በሽታን ተይዘው ተርፈዋል እናም ይህ የሆነው በመጠነ ሰፊ ህከምና ፣ ሚልዋዪኪ ፕሮቶኮልተብሎ በሚጠራው ነው።[4]

የእብድ ውሻ በሽታ በአለም ዙሪያ በአመት ከ26,000 እሰከ 55,000 ሞቶች ምክንያት ነው።[1][5] ከ95% በላይ እነዚህ ሞቶች የተከሰቱት በኢሲያ እና አፍሪቃነው።[1] የእብድ ውሻ በሽታ ከ150 ሀገራት በላይ እና ከአንታርቲካ በቀር በሁሉም አሀጉራት ይገኛል። [1] ከ3 ቢሊዮን ሰዎች በላይ የእብድ ወሻ በሽታ በሚከሰትበት የአለማችን ከፍሎች ውስጥ ይኖራሉ።[1] እጅግ በአብዛኛው አውሮፓ እና አውስትራሊያ፣ የእብድ ወሻ በሽታ የሚገኘው በሌሊት ወፎች ላይ ነው። [6] በዙ ትናንሽ የደሴት ሀገራት ጭራሹን የእብድ ውሻ በሽታ የለባቸውም።[7]

ዋቢ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Rabies Fact Sheet N°99". World Health Organization (July 2013). በ28 February 2014 የተወሰደ.
  2. ^ Cotran RS, Kumar V, Fausto N (2005). Robbins and Cotran Pathologic Basis of Disease (7th ed.). Elsevier/Saunders. p. 1375. ISBN 0-7216-0187-1. 
  3. ^ Tintinalli, Judith E. (2010). Emergency Medicine: A Comprehensive Study Guide (Emergency Medicine (Tintinalli)). McGraw-Hill. pp. Chapter 152. ISBN 0-07-148480-9. 
  4. ^ Hemachudha T, Ugolini G, Wacharapluesadee S, Sungkarat W, Shuangshoti S, Laothamatas J (May 2013). "Human rabies: neuropathogenesis, diagnosis, and management.". Lancet neurology 12 (5): 498–513. doi:10.1016/s1474-4422(13)70038-3. PMID 23602163. 
  5. ^ Lozano R, Naghavi M, Foreman K, Lim S, Shibuya K, Aboyans V, Abraham J, Adair T, Aggarwal R, et al. (Dec 15, 2012). "Global and regional mortality from 235 causes of death for 20 age groups in 1990 and 2010: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2010.". Lancet 380 (9859): 2095–128. doi:10.1016/S0140-6736(12)61728-0. PMID 23245604. 
  6. ^ "Presence / absence of rabies in 2007". World Health Organization (2007). በ1 March 2014 የተወሰደ.
  7. ^ "Rabies-Free Countries and Political Units". CDC. በ1 March 2014 የተወሰደ.

0900968359 or 0934413051