የውሃ ኡደት
Appearance
የውሃ ኡደት ማለት በሰማይ፣ በምድር ላይ እና ከምድር በታች ያለው የማያቋርጥ የውሃ እንቅስቃሴ ማለት ነው። ውሃ እየተነነ፣ እየጤዘ፣ እየዘነበ፣ እና ከምድር ውስጥ እየሰረገ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላው ይዘዋወራል። በሚዘዋወርበትም ጊዜ ከፈሳሽነት ወደ በረዶ እና ጋዝ ይለዋወጣል። በዚህም መልክ ውሃ ሲዘዋወር ውሃው ይጣራል፣ ጨው አልባ ይሆናል፣ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችንም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያመላልሳል። በተጨማሪም ድንጋይን በመሸርሸር እና አፈርና አሸዋ በማዝቀጥ የዓለምን መልክዓ ምድር ይለውጣል።
የውሃ ኡደት ኃይል /energy/ መለዋወጥን ያካትታል። ይህም የሙቀት ልክ ከፍና ዝቅ እንዲል ያደርጋል። ለምሳሌ፦ ውሃ ሲተን ኃይል ስለሚወስድ አካባቢውን ያበርዳል።