የዓሣ ጉላሽ በሩዝ
Appearance
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 8 መካከለኛ ጭልፋ (800 ግራም) በትልቁ የተከተፈ ተላፒያ ዓሣ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቲማቲም
- 3 ፍሬው ወጥቶ የተከተፈ ቃርያ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
- 4 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
- 4 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- 4 መካከለኛ ጭልፋ (250 ግራም) የተቀቀለ ሩዝ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- 1. ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ማቁላላት፤
- 2. ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
- 3. የቲማቲም ድልህ ጨምሮ ማዋሃድ፤
- 4. የተከተፈውን ቲማቲም መጨመርና በደንብ እስኪበስል ማንተክተክ፤
- 5. ከላይ በተሠራው ሶስ ዓሣውን፣ ቁንዶ በርበሬና ጨውን ጨምሮ ማማሰል፤
- 6. ሲበስል ቃርያ ነስንሶ ከሩዙ ጋር ቀላቅሎ ማቅረብ፡፡