የዓባይ ልጅ

ከውክፔዲያ

የዓባይ ልጅ


የጣልቃ ገብነት መሳሪያው በኢትዮጵያ

         

    እስሌማን ዓባይ✍️

[ቃል በገባሁት መሰረት፡ አንድ የሀገራችን ተቋም ከUSAID ታብሌት መረከቡ፤ እንዲሁም በተያያዥ የሚመጣ ስውር አጀንዳ የፅሁፉ ትኩረት ይሆናል። ከተቋሙ አመራሮች ጋር ስለ ስጋቱ በመነጋገራችን ስሙን ባለመጥቀስ አቅርቤዋለሁ።

መስሪያ ቤቱ ታብሌቶቹን የተቀበለው ከUSAID የባሰ ከሆነው የፔንታጎን ቅርንጫፍ መሆኑ ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል። ይህ የUSAID ቅርንጫፍ የሽግግር ኢኒሼቲቭ ቢሮ ይባላል፣ Office of Transitional Initiative ወይም ITO የሚሉት።

የUSAID የውጭ ተልዕኮ ከሌሎች ዘመናት በተለየ እንዲሆን ባይደን ማዘዛቸው ይታወሳል። ይኸውም በሳማንታ ፓወር እየተመራ ከመቼውም በበለጠ የCIA ቀኝ እጅ እንዲሆን ነበር የተደረገው።

ለኢትዮጵያው ተቋም ታብሌቶች ያቀረበው OTI  አደገኛው የUSAID ክንፍ ሲሆን በውጭ አገራት እንደ ጦርነት አይነት ቀውስ ሲከሰት የሚቋቋም ነው። OTi ምን ሲያደርግ ነበር? ብለን ስንጠይቅ ምላሹ በምንገምታቸውም በማንገምታቸውም ተንኮሎች የተሞላ ታሪኩን እንሰማለን። ልብ በሉ ስጋተለ የኛው ተቋም ታብሌት ከመቀበሉ በላይ በሶስቱ ክልሎች usaid ካቀረበው የርዳታ ገንዘብ ጋር አብሮ የሚመጣ ጣጣ ነው።

መሰል ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ከውጭ አገራት መቀበላችን አይቀሬ ነውና የሳይበር ጥበቃ firewall አቅም መገንባት የመፍትሄ አንዱ ርምጃ ነው። ይሁንና ቁልፍ መረጃዎችና የመረጃ ሰዎች ጋር ልውውጥ የሚያደርግ የአገራችን መስሪያ ቤት ከተቀበለው የታብሌት ርዳታ ከጥቅሙ አሉታዊ ጉዳቱ እጅጉን አሳሳቢ ይሆናል።

ከ33 ታብሌቶች ድጋፍ በተጨማሪ ባለፈው አመት ከOTI የትብብር ስምምነት አድርገው አራት አማካሪዎችን ወጪ ሸፍኖ አስመድቧል። ሰባት ተለማማጅ ባለሙያዎች ቅጥርና የቁሳቁስ ግዢ በአጠቃላይ 100 ሺህ ዶላር/3.8 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉን በድረ ገፁ አስፍሯል።

  ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ፣ መሳሪያውን እሺ ብሎ የተቀበለው መስሪያ ቤት በመሰል ስጋቶችን በተመለከተ ጥናታዊ ምክረ-ሐሳቦች እንዲያቀርብ የተመሰረተ መሆኑ ነው።

OTI ማነው?

የዛሬን አያርገውና የOTI ጉድ ይፋ የሆነው በአሶሼትድ ፕሬስ የምርመራ ዘገባ ነበር። አሶሼትድ ፕሬስ መረጃውን ደልቶታል፤ ኮፒዎችን ግን ማግኘት ችያለሁ።

በወቅቱ ሶስት የAP ጋዜጠኞች በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እኛ በዩኤስኤአይዲ በኩል በተከፈተ የሽግግር ተነሳሽነት ቢሮ OTI በሚል ግልጽ ያልሆነ ቢሮ በኩባ የሞባይል ስልኮች ትዊተርን የመሰለ የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያ ለCIA አላማ ማስፈፀሚያነት ስለማዘጋጀቱ ምርመራ ዘገባው ፀሀይ ላይ አስጥቶት አልፏል።

የኩባ ወጣቶች መተግብሪያው በአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች እንደሚሾር፣ ግላዊ መረጃቸው እየተቀዳ መሆኑን አልጠረጠሩም ነበር ይላል ዘገባው። "ZunZuneo" በማለት በኩባ ብሄራዊ ወፍ የተሰየመ መተግበሪያ

“usaid" የኩባዊያንን የግል መረጃ ይሰበስባል፣ በሚፈጥሩት መስተጋብርም የፖለቲካ ዝንባሌዎቻቸውን በደረጃ ያስቀምጣል። "የኩባ መንግስትን የሚቃወሙ ባንዶች በ..ኮንሰርቱ ላይ እንዲጫወቱ መፍቀድ ተገቢ ነበር ወይ?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር የምርመራ ዘገባው በአብነት ተጠቅሶታል።

ስትራቴጂ በወጣቱ የሚወደዱ መረጃዎችን መጀመሪያ ላይ በስፋት በማቅረብ፣ በሂደት የተመዝጋቢውንና የተሳትፎ መጠኑን መገንባት፣ ቀስ በቀስ ደግሞ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጉዳዮችን በማቅረብ ኋላ ላይም ወደ ፖለቲካዊ ንቅናቄ እንዲገቡ ማነሳሳት ነበር። በዚህም በመንግስትና ህብረተሰቡ መሀል ያለውን የሃይል ሚዛን መናድና በሚፈለገው መንገድ እንደገና ለማዋቀር ያለመ ነበር። እንደ ምርመራ ሪፖርቱ።

አብዛኛዎቹ የዩኤስኤአይዲ የጣልቃ ገብነት ፕሮጄክቶች “ሽግግር” ብለው በሚጠሩት ስያሜ በOTI በኩል ነው ተፈፃሚ የሚሆኑት። በ1994 የተመሰረተው OTI በራሷ በአሜሪካ ከሚገኙ የባንዳ ኔትወርኮች፣ የልማት ድርጅቶችና “መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት” ተብዬዎች ጋር ውል ገብቷል በሚል ተወግዟል።

OTI ከusaid ጋር ሲሰራ ከሲአይኤ በስተቀር ከየትኛውም የልማት ድርጅቱ ክንፍ ወይም የመንግስት አካል የተነጠለ አካሄድ ያለው ነው። 

“OTI ልዩ የአስተዳደር ዘይቤ ያለውና እንደ CIA የውጭ ዘመቻ በተለየ የተቋቋመ ቢሮ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል።  ይህ የአስተዳደር ዘይቤ በኦቲአይ እና በኮንትራክተሩ መካከል በሚኖር ጠንካራ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ይሆናል”።

"ዓላማው...የሽግግር ተነሳሽነት ቢሮ (ኦቲአይ) ለአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ አላማ ቀውስ የገባችው ሀገር ውስጥ የሚገኙ አጋሮችን በመርዳት... የሽግግርና የማረጋጊያ ፍላጎቶች ላይ ያነጣጠረ ፈጣን፣ ተለዋዋጭ፣ የአጭር ጊዜ ርዳታ በመስጠት ይሰራል።

"በሽግግር፣ በግጭት ወይም ከግጭት ወደ ሰላም እንዲሁም መሰል ወሳኝ የፖለቲካ ክንውኖች ሲከሰቱ OTI የእድል መስኮቱን የሚታወቅበትን የአጭር ጊዜ ፕሮጀክት ይጀምራል። አብዛኛውን ጊዜ እስከ ሶስት አመት የጊዜ ቆይታ ያለው ነው”

ወደ አንድ ሀገር ከመግባታቸው በፊት ተከታዮቹን መመዘኛዎች ይጠቀማል፡-

“ • አገሪቱ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ናት?

• አሜሪካን የሚጠቅም የእድል መስኮት አለ?

• የኦቲአይ መሳተፍ ለአሜሪካ ጥቅም የመሳካቱን እድል በከፍተኛ ደረጃ መጨምር ይችላል?

ይኸው የOTI ቢሮ የመጀመሪያውን መስፈርቱን እንደሚከተለው ያብራራል።

“ • አገሪቱ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ጠቃሚ ናት?  ሰብአዊ ርዳታ የሚከፋፈለው በተረጂ መንግስታት ፍላጎት ላይ ብቻ ቢሆንም፣ የOTI የሽግግር/ቀውስ ርዳታ የሚመደበው የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ ዓላማዎችና አንገብጋቢ ጉዳዮች ለማራመድ በማሰብ ነው”።

በተጨማሪም ዩኤስኤአይዲ ሰራተኞች ለመሄድ በማይደፍሩባቸው አካባቢዎች ኦቲአይ ልክ እምደ ሲአይኤ ተጎዞ ጉዳዩን ይፈፅማል።

ከOTI ጋር በኮንሰልታንትነት ለመስራት ከፍተኛ የደህንነት ማረጋገጫ የሚጠይቅ ሲሆን ከ"ልማት ድርጅቶች" የሚያደርጋቸው ውሎችም ብዙ ጊዜ ከፔንታጎን "የኮንትራት ደህንነት ምደባ ዝርዝር" የሚል አባሪ የሚሰጣቸው ናቸው።

ይህ ጉድ በAP የምርመራ ዘገባ ከተጋለጠ በኋላ በኤፕሪል 8 2014፣ አሜሪካዊው ሴናተር ፓትሪክ ሌሂ ፕሮጀክቱን “ደደብ፣ ደደብ፣ ደደብ” ብለው ነበር የገለፁት።

ለማሰተባበል ለሞከረው የUSAID ስራ ሀላፊ ከሌላኛው ባለስልጣን የተሰጠው ምላሽ “ሁሉንም የዩኤስኤአይዲ ሰራተኞች ሰላይ ብሎ ለመፈረጅ አያስችልም' የተባለው ተራ ማስተባበያ ነው።" ያሉ ሲሆን "በሁሉም ሀገር የተመደቡ የUSAID ሰራተኞች ለኛ ለሴናተሮች በሚልኩት አንድ አይነት የቅሬታ ኢሜይላቸው 'እንዴት እንዲህ አይነት አደጋ ላይ ይጥሉናል?” ነው የሚሉት.." በማለት ድርጊቱ ድሮም በበጎ የማይነሳውን የአሜሪካ ስም ይበልጥ የሚያጠለሽ ድርጊት ነው..በማለት አፍረንባችኋል ብለዋቸዋል።

በOTI ተቀጥረው የሚገኙ የሀገራችን ዜጎች ከተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው እየፈለግኩ ተመለከትኳቸው። ምናልባትም እነሱ ሳያውቁት መጠቀሚያ እየተደረጉ ይመስለኛል።

ዋናው ነጥብ፣ የዚህ የOTI ዋና ኢላማ ታብሌት የተቀበለው ተቋም አይደለም። USAID ለተለያዩ ክልሎች ካቀረበው የቢሊዮን ብሮች የልማትና ስራ ፈጠራ ርዳታ ውስጥ ግማሹ የOTI አጀንዳዎችን የሚመለከቱ መሆናቸውን አንብቤያለሁ።

Esleman abay #የዓባይልጅ