Jump to content

የዓፄ ምኒልክ ደብዳቤ

ከውክፔዲያ

የዓፄ ምኒልክ ደብዳቤ፦ (ደብዳቤ ቊጥር ፩ ሺ ፯፻፲፭ 1715)

ይድረስ ከራስ ሚካኤል

ይህ ፋሪስ ወልደ ማርያም የሚባለው ቦረና ነገሌ የደጃዝማች ካሣ አሽከር ቤቴ ተቃጥሎ ሌባ ሻይ ቢያመጣ እኔ ቤት ተኛ። እኔም በራስ ሚካኤል ቃል አስደግሜ ተመልሶ እዚያው ተመልሶ ተኛ። ይህንኑ ለአፈ ንጉሥ ነሲቡ ጮኬ ከሰይዱ ጋር አጋጥመውኝ ሌባ ሻዩም ሁለት ግዜ አንተው ቤት ከተኛ ክፈል ብለውኝ ቤቴ ሠላሳ ብር ርስቴ አራት ብር ያወጣል ቢሉኝ እንደገና ጮኬ የአገር ሽማግሌ ጎረቤት በገመተው ክፈል በሚል ለአፈ ንጉሥ ማኀተም ወስጄ ሽማግሌ በገመተው ክፈል በሚል ለአፈ ንጉሥ ማኅተም ወስጄ ሽማግሌ በገመተው ልክፈል ሁለት ዋስ ጨርቼ እንገማመት ሳይለኝ ከርሞ አሁን በዓመቱ ከአፈ ንጉሥ ነሲቡ ማኅተም አላወጣም ብሎ ከሶ ማኅተሙም ራስ ሚካኤል ዘንድ ጠፋ። ከዋሶቹ ሠላሳ አራት ብር ተቀበሏቸው። ይህንኑም እንደገና ጮኼ ማ[ኅ]ተም አምጣ አሉኝ ብሏልና ከዋሶቹ የተበላ ሠላሳ አራት ብር ይመለስና የአገር ሽማግሌ ቤቱን የሚያውቅ ጎረቤት በገመተው ይክፈል።

ሐምሌ ፴ ቀን ፲፱፻ ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ።

ምንጭ፦ ከሣቴ ብርሃን ቡሩክ ከጳውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች ከሚል መጽሐፍ ላይ ገልበጠው እንደተየቡት