የደበኔ ሳጥን መርህ
Appearance
የደበኔ ሳጥን መርህ እሚለው a ነገሮች b ሳጥኖች ውስጥ ቢቀመጡ፣ የነገሮቹ ብዛት ከሳጥኖቹ ብዛት ቢበልጥ a > b፣ አንዱ ሳጥን ሁለት ነገሮችን የግዴታ ይዟል።
ምሳሌ፡ አንድ ሻንጣ ውስጥ 12 ሰማያዊ ካልሲዎችና 18 ጥቁር ካልሲወች አሉ። አይናችንን ጨፍነን ስንት ካልሲ ከሳጥኑ ብናወጣ የግዴታ አንድ አይነት ቀለም ያላቸው ሁለት ካልሲዎች ልናገኝ እንችላለን? ለአንዱ ቀለም አይነት አንድ ሳጥን ብናበጅ እና ለሌላው አንድ ሳጥን ብናበጅ፣ ሁለት ሳጥን በቀለሞች አሉን። ሶስት ካልሲዎች ብናወጣ የግዴታ ሁለቱ አንዱ ሳጥን ውስጥ መውደቅ አለባቸው (አንድ አይነት ቀለም መሆን አለባቸው)፣ ስለሆነም መልሱ 3 ነው ማለት ነው።