የደንጣ፣ ዱባሞ ክንችችላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
በለውጡ መንግሥት ሰሚ ያጣ ጩኸት
#በጨቋኙ በሀዲያ ዞን
✍!✍!✍✍✍✍✍✍✍!
#የደንጣ ብሄረሰብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን ይህ ብሄረሰብ የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል እና አንድ ወጥ የሆነ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው ህዝብ ነው።
#የደንጣ ህዝብ በ1984 ዓ/ም ማንነቴ ይታውቅልኝ ጥያቄ ንቅናቄ በማድረግ በጊምቢቹ ከተማ መዝናኛ እስቴዲየም ህዝባዊ ብሄራዊ ስብሰባ በማድረግ (ደዱክህድድን) ወይም የደንጣ ዱባሞ ክንችችላ ህዝባዊ ዲሞክራሳዊ ድርጅት ንቅናቄ የሚባል የፖለቲካ ድረጅት መመስረቱ ይታወቃል።
#የደንጣ ህዝብ ይህን ፓርቲ ከተመስረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረሰ ማንነቱ ታውቆ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅናውን እንዲሰጠው ሲል ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሲታገል ድፍን 32 አመታትን ያሰቆጠር ትግል ሲታገል የቆየ ጨዋ ህዝብ ነው።
ቢሆንም ግን የደንጣ ህዝብ ይሄንን የማንነቱን ጥያቄ መጠየቁን ያልተዋጠለት የሀዲያ ዞን መስተዳደር የሆነው በትግላችን ላይ የተለያዩ ሴራዎችን በመፍጠር እስከ ዛሬ ድረሰ ጥያቄያችን ሳይመለስልን በእንጥልጥል እንዲቆይብን አድርጎብናል።
#እንደዚሁም ማንነቴ ይታውቅልኝ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ በአመራር ደረጃ ተመርጠው እስከ ዛሬ ድረሰ ሲንገላቱ የኖሩት የደንጣ ህዝብ የማንነት ጥያቄ አስመላሽ ኮሚቴ ጥያቄዉን ከወረዳው ምክር ቤት ጅምሮ ለሀዲያ ዞን ጽ/ ቤት ለደቡብ ክልል ምክር ቤት እንደዚሁም ለኢትዮጲያ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለሚመለከተው ክፍል አካል በሙሉ የደንጣ ህዝብ ማንነቴ ይታውቅልኝ ጥያቄ በማቅረብ እና በመጠየቅ እስከ ዛሬ ድረስ እየጮህ ይገኛል።
በነዚህ በደንጣ የማንነቴ ይታውቅልኝ ጥያቄ አስመላሽ ኮሚቴዎች ላይ ይሄንን ጉዳይ ይዘው ወደ ሚመለከተቸው አካለት በመንቀሳቀሳቸው በዚህ ሰበብ ብቻ የብዙ ችግር ሰለባዎች በመሆን ጥያቄው ከዛሬ ነገ ምላሽ ያገኛል በሚል ሀሳብ ሲጠባበቁ ለጥያቄው ምላሽ ሳይሰጠው ዛሬም ቀን እየቆጠረ ይገኛል።
#የደንጣ ህዝቡ በተደጋጋሚ የሚጠይቀውን፣ ህገ መንግስታዊ መብቱ የሆነውን እና ህዝባዊ መሰረት ያለውን በማንነት የመታወቅ እና የመደራጀት ጥያቄውን በጉልበት ለመጨፍለቅ መሞከር እና ያልሆነውን ነህ ተብሎ በጉልበት የደንጣ ህዝብ ማንነቱን የመጨፍለቅ ስራ ለመስራት የሚሯሯጡት የሀዲያ ዞን የክልሉ ባለስልጣናት አንድ ሊባሉ ይገባል።
#የደንጣ ህዝብ በሀዲያ ብሄርሰብ መጨፍለቅን ጠልቶ አደባባይ እስከ ወጣ ድርስ ለህዝቡ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ መስጠት እና የልብ ትርታውን ማዳመጥ የሀዲያ ዞን መስተዳደር ሆነ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች እንዲሁም የመንግስታት ሃላፊነት እንደሆነ የተገነዘቡት አይመስለኝም።
#የደንጣ ብሄረሰብ በቅርበት የሚያውቁት ማንኛውም ሰው የተለየ የራሱ የሆነ ቋንቋ ባህል እና የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም ማንነት እንዳለው እና እንደ ብሔረሰብ መደራጀትም ሆነ መታወቅ እንደሚገባው ያምናሉ።
#የደንጣ ህዝብ የማንነት ጥያቄን ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርቡ ማህበረሰቡ የመረጣቸዉ ምሁራንና ሹማግሌዎች ለደቡብ ክልል ምክር ቤቶች እና ኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት እና ለሚመለከታቸዉ ተቋማት ለሁሉም ለዓመታት ሲያቀርቡ ቢቆዩም ጥያቄው በፓለቲካ አሻጥር ሲያሹት እና ሲያስተጓጉሉት አቆይተውታል።
#የደንጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ ማቅረቡ በአሉታዊ መልኩ በመውሰድ የሀዲያ ህዝብ ቁጥር እንደሚቀንስ እና ተፅዕኖ እንደሚፈጥር አድርገው የሚያስቡ ሰዎች ወደ ቀልባቸው ቢመለሱ የተሻል ሀሳብ ይሆናል ብዬ አምናለሁኝ።
#ምክንያቱም የደንጣ ህዝብ ሰው አክባሪ፣ ስራ ወዳድ ነው
የደንጣ፣ ጎሳ የደንጣ ብሔር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጎሳዎችን የያዘ ነው ።
1. ጎጅና 28. ደሞዞ
2. ዘዋሪ 29. ወንጌሎ
3. ዶለ 30. ጀንጄቾ
4. ጉለ
5. ጉጅያ
6. ክንቺቺለ
7. ጎሎንጃ
8. ወሰኖ
9. ከተሞ
10. ቦኖሶ
11. ኬሌቶ
12. ተውሎ
13. ገሬኖ
14. ገቡሮ
15. ፋጄ
16. እዚጌሮ
17. ወበዞ
18. አጀሮፈ
19. ሀተፋራ
20. ደቦና
21. ገራሶ
22. ሱዋኮ
23. ወሼ
24. ሲቆ
25. ሲሶ
26. ሻሞ
27. ኦቶ
ምን ነበር ዓላማው??
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
ደንጣ ማለት በሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ ውስጥ የምገኝ ቀበሌ ነው።
በዛ አከባቢ የምኖሩ በከፍል በጣሊያን ወረራ ጊዜ ታቦት ይዞ የፈለሱ የሰሜን ሰዎች ይገኛሉ ።
የሀዲያ ህዝብ እንደምታወቀው ኢስላማዊ ሱልጣኔት ነበር በዚያን ወቅት ዱባሞ እና ቤተሰቦቹ ሀዲያን ለማስገበር፣ ክንችችላና ቤተሰቦቹ ከጣሊያን ጦርነት ሽሽት እና ሃይማኖት ለማስፋፋት የፈለሱ ስሆን ሁለቱም ቤተሰቦች በዚያው ወቅት የሀዲያ መንግሥት ኢስላማዊ መንግስትና ጠንካራ የጦር ኃይል ስለነበረ በሀዲያ ጦር ቁጥጥር ስር ውሎ ከተማረኩ በኃላ የጦር መሳሪያ በመቀማት የሀዲያ ንጉስ ለእነዚህ ምርኮኞች መሬትና ንብረት በጊዜያዊነት ሰጥቶ ይኖሩ ነበር በህደትም ከሀዲያ ህዝብ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ መኖር ጀመሩ የሀዲያ በህልና ቋንቋውንም ለመዱ ከሀዲያም ሴት ልጆቻቸውን አግብቶ ዘራቸውን አበዙ ከመዋደዳቸውም የተነሳ ያኔ በጣት የምቆጠሩ ሰዎችን ከሀዲያ አንድ ጎሳ ተብሎ እንድጠሩ ተደረገ ።
የሀዲያ ህዝብ አፍቃሪ፣ አቃፍ፣የምራራና የዋህ ህዝብ ነው ለዚህም ማሳያ ከሰሜን ልዋጋ የመጣውን ክንችችላና ዱባሞ እንደ አንድ ልጅ ተንከባክቦ ያኖራል ።
ደንጣ ማለት በሀዲያ ዞን ውስጥ በሶሮ ወረዳ የምገኝ የአንድ ቀበሌ ስም ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! (11/09/2016) |