የዶሮ አሮስቶ

ከውክፔዲያ

የዶሮ አሮስቶ (ሮስትድ ቺክን) ለ2 ሰው

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች - 1 በደንብ የፀዳ ዶሮ (ከ800 ግራም እስከ 1 ኪሎ ግራም የሚመዝን) - ሩብ ሊትር ዘይት - 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ቺክን ስቶክ

- 10 የሾርባ ማንከያ ብሬድ ሶስ - 1 የሻይ ማንኪያ ጨው - 3 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ሮዝመሪኖ - 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ - 1 የሻይ ማንኪያ በርበሬ - 1 የሻይ ማንኪያ ሰናፍጭ (መስታርድ) - 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት

አዘገጃጀት


1. ቁንዶ በርበሬ፣ በርበሬ፣ ሮዝመሪኖ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ሰናፍጭና 6 የሾርባ ማንኪያ ዘይት ደባልቆ መለወስ፤ 2. የዶሮውን ውስጣዊና ውጫዊ አካል በተዘጋጀው ዉሁድ እያሹ መቀባት፤ 3. በብረት ምጣድ ወይም በድስት ውስጥ ትንሽ ዘይት አግሎ እያገላበጡ ወርቃማ መልክ እስኪያወጣ መጥበስ፤ 4. ቀሪውን ዘይት የዳቦ መጋገሪያ በትሪ ላይ አግሎ ዶሮውን ላዩ ላይ ማድረግ፤ 5. ዳቦ መጋገሪያ ውስጥ መክተት፤ 6. እያገላበጡ የራሱን መረቅ ከላይ በመጨመር ማብሰል፤ 7. ዶሮውን አውጥቶ ቺክን ስቶኩን በላዩ ጨምሮ በማማሰል ወፈር ብሎ ሲንተከተክ ማውጣት፤ 8. ጨዉንና ቅመሙን አስተካክሎ በጠቅጣቃ ማጥለያ ማጥለል፤ 9. የተዘጋጀውን (ሶስ..ና ብሬድ ሶሱን ለየብቻ በማድረግ የዶሮ አሮስቶውን ለሁለት ከፍሎ ማቅረብ፡፡


(ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ)፤ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 1993)