የዶሮ ክሬም ሱፕ

ከውክፔዲያ

ቺክን ክሬም ሱፕ (ለ10 ሰው)

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች  3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በስሎ የተገረደፈ የዶሮ ስጋ  1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) ደቆ የተከተፈ የባሮ ሽንኩርት  1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ የሲለሪ ግንድ  5 የሾርባ ማንኪያ ፉርኖ ዱቄት  1 ሊትር ወተት  4 ሊትር ቺክን ስቶክ (የዶሮ መረቅ)  ቡኬጋርኒ  1 የሻይ ማንኪያ ጨው  1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ  3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ

አዘገጃጀት 1. ቅቤውን በወፍራም ብረት ድስት ማቅለጥና ማሞቅ፣ 2. ሽንኩርት፣ ባሮና ሲለሪውን መጨመር፣ 3. እንዳይቀላ በጥንቃቄ ማብሰል፣ 4. ዱቄቱን ጨምሮ ነጣ ያለ አሸዋማ መልክ ቀለም እስኪያወጣ በደንብ ማማሰል፣ 5. መረቁን አሙቆ ጠብ እያደረጉ እንዳይጓጉል በማማሰል መረቁን ጨርሶ መጨመር፣ 6. እስኪፈላ እንዳይዝ አልፎ አልፎ ማማሰል፣ 7. ቡኬጋርኒውን ጨምሮ ማማሰል፣ 8. ጨውን ማስተካከልና ቁንዶ በርበሬውን መጨመር፣ 9. እንዲፈላ መተው፣ 10. መካከለኛ ውፍረት እስኪያገኝ ድረስ ማቆየት፣ 11. ቡኬጋርኒውን ማውጣት፣ 12. በማጥለያ ካጠለሉ በኋላ መልሶ ጥዶ ወተት መጨመር፣ 13. የዶሮውን ስጋ ጨምሮ ማቅረብ፡፡