የዶሮ ጥብስ በከሰል
Appearance
- ከ1 ኪሎ እስከ 1 ½ ኪሎ የሚመዝን ዶሮ
- 1 ራስ ቀይ ሽንኩርት
- 2 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ጭማቂ
- 1 የሻይ ማንኪያ የሥጋ ቅመም (ታይም ወይም በሶብላ)
- 2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ ኮምጣጤ
- 1 የሻይ ማንኪያ ሶያሶስ
- ½ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- ዶሮው ተቆራርጦ (ያለ ቆዳ) በደንብ ከታጠበ በኋላ አጠንፍፎ ትልቅ ድስት ውስጥ መጨመር፤
- ሽንኩርት በርዝመቱ ከታትፎ በላዩ ላይ መጣል፤
- ጨውና ቅመሙን መነስነስ፤
- ያንን የቲማቲም ጭማቂ፣ የዘይት፣ የኮምጣጤና የሶያሶስ ድብልቅ ውስጥ ለአንድ ሰዓት ያህል መዘፍዘፍ፤
- እያወጡ በብረት ሽቦ ላይ በከሰል ላይ መጥበስ (እሳት ሳይበዛበት ተስተካክሎ በጥንቃቄ መብሰል አለበት።