የጋራ ስብስብ
Appearance
የሁለት ስብስቦችን የጋራ አባላት በመውሰድ እንዲሁ አዲስ ስብስብ መፍጠር ይቻላል። የA እና B የጋራ ስብስብ እንዲህ ይወከላል A ∩ B,፤ ትርጓሜውም በ A እና በ B ውስጥ የሚገኙ የጋራ አባላቶች ስብስብ ማለት ነው። A ∩ B = ∅, ከሆነ A እና B የየቅል ስብስብ ይሰኛሉ።
ምሳሌዎች:
- {1, 2} ∩ {ቀይ, ነጭ} = ∅.
- {1, 2, አረንጓዴ} ∩ {ቀይ, ነጭ, አረንጓዴ} = {አረንጓዴ}.
- {1, 2} ∩ {1, 2} = {1, 2}.
የጋራ ስብስብ መሰረታዊ ጸባዮች:
- A ∩ B = B ∩ A.
- A ∩ (B ∩ C) = (A ∩ B) ∩ C.
- A ∩ B ⊆ A.
- A ∩ A = A.
- A ∩ ∅ = ∅.
- A ⊆ B የሚሆነው A ∩ B = A. ከሆነና ከሆነ ብቻ ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |