የግሪክ አልፋቤት
Appearance
የግሪክ አልፋቤት ቢያንስ ከ800 ዓክልበ. ጀምሮ ግሪክኛን ለመጻፍ ተጠቅሟል። የተደረጀው ከፊንቄ ጽሕፈት ሲሆን የአንዳንዱ ፊደል ጥቅም ከተነባቢ ወደ አናባቢ በመለወጡ የግሪክ አልፋቤት መጀመርያው የአናባቢ ፊደል ጥቅም ያገኘው ጽሕፈት ሆነ። የግሪክ አልፋቤትም በተለይ ለላቲን አልፋቤትና ለቂርሎስ አልፋቤት፣ ለሌሎችም፣ ወላጅ ሆነላቸው። ከግሪክኛ በላይ የግሪኩ ጽሕፈት ለአንዳንድ ሌሎች ልሳናት ተለምዷል።
በዘመናዊ ግሪክ ቋንቋ በጥቅም ላይ የሚውሉት ፊደላት እነዚህ ናቸው።
|
|
- ምሳሌዎች
የግሪክ አልፋቤት ከ800 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ቢታወቅም ከዚያ በፊት ከ1450 እስከ 1100 ዓክልበ. ድረስ ባለው ጊዜ በሚውኬናይ ጽሕፈት የተጻፉ ቅድመ-ግሪክኛ መዝገቦች ከሥነ ቅርስ ተገኝተዋል።
- ^ ሀ ለ Woodard 2008, pp. 15–17
- ^ ሀ ለ Holton, Mackridge & Philippaki-Warburton 1998, p. 31