የጡት ካንሰር
የጡት ካንሰር በሽታ በጡት ላይ ከሚከሰት ካንሰር የሚመጣ ነው። የማንኛውም ጤናማ ሰው ሴሎች በየጊዜው ያድጋሉ ይለዋወጣሉ። ይህ የሴሎች እድገት ጤናማ ባልሆነ መልኩ እየጨመረ ሲሄድ እብጠትን (ዕጢ) ያስከትላል። አንዳንድ እብጠቶች በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰርነት ይለወጣሉ። [1]
የጡት ካንሰር በሚከሰትበት ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ይመስላሉ።[2]
- በጡት ላይ የሚከሰት እብጠት
- ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከጡት መዉጣት
- የጡት ቆዳ ወደ ዉስጥ መሰርጎድ
- የጡት ወይም የጡት ጫፍ ህመም
- የጡት ጫፍ ወደ ዉስጥ መግባት
- የጡት ቆዳ ቀለም ወደ ቀይነት ማድላት
- የጡት ቆዳ መሻከር
ለጡት ካንሰር እንደ መንስኤነት ከሚነሱ ነገሮች መካከል
- ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት፣[3]
- የእድሜ መጨመር፣
- የጡት ካንሰር የቤተሰብ ታሪክ
- አልኮል መጠጣት
አንድ ሰው በጡት ካንሰር እንደተጠቃ ለማወቅ የህክምና ባለሙያዎች ከሚያደርጓቸው የምርመራ ሂደቶች ውስጥ የማሞግራፊ ፣ አልትራሳውንድ ምርመራዎች ናቸው።
የጡት ካንሰር በስፋት የሚታየው ሴቶች ላይ ቢሆንም በወንዶችም ላይ የመከሰት እድል ግን አለው። [4]
የጡት ካንሰርን ለማከም የተለያዩ እርምጃዎች የሚወሰዱ ሲሆን እነዚህ እርምጃዎችም ካንሰሩ እንደ ደረሰብት ደረጃ እና የበሽተኛው ሁኔታ ሊለያዩ ይችላሉ። የቀዶ ጥገና ፣ ኬሞቴራፒ ፣ ሆርሞናዊ ቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ናቸው።[5] የቀዶ ጥገና ህክምና ካንሰሩን ሙሉ በሙሉ ማውጣት ወይም ሙሉውን ጡት መቆረጥ ሊያካትት ይችላል። ከዚያ በኋላ አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ ኬሞ እና ራዲዮቴራፒ ያስፈልጋቸዋል። በአንጻሩ ደግሞ የኬሞቴራፒ ህክምናመድኃኒቶች የበሽታውን መስፋፍት የሚከላከሉ እና ተመልሶ እንዳይመጣ የሚያረጉ መድኃኒቶች ሲሆኑ እንደ አይነታቸው የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶች አላቸው። የኬሞቴራፒ ሕክምና አሰጣጡ እንደ ጡት ካንሰሩ አይነት እና ደረጃ የሚወሰን ነው።
በሽታው ከመከሰቱ በፊት ሊወሰዱ ከሚችሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች መካከል በየጊዜው ምርመራ ማድረግ ፣ ከወሊድ በኋላ ጡት ማጥባት፣ የአልኮል መጠጥ መቀነስ ይገኑበታል።
የጡት ካንሰርን አስከፊነት እና መከላከያ ዘዴዎቹን በተመለከተ ግንዛቤ ለማስጨበት በየአመቱ በጥቅምት ወር የጡት ካንሰር ቀን ይከበራል። [6]
- ^ https://yetenaweg.com/%E1%8B%A8%E1%8C%A1%E1%89%B5-%E1%8A%AB%E1%8A%95%E1%88%B0%E1%88%AD-2/
- ^ https://drabduadem.com/%E1%8B%A8%E1%8C%A1%E1%89%B5-%E1%8A%AB%E1%8A%95%E1%88%B0%E1%88%AD-%E1%88%9D%E1%88%8D%E1%8A%AD%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%88%9B%E1%88%A8%E1%8C%8B%E1%8C%88%E1%8C%AB-%E1%88%98%E1%8A%95/
- ^ https://yetenaweg.com/%E1%8B%A8%E1%8C%A1%E1%89%B5-%E1%8A%AB%E1%8A%95%E1%88%B0%E1%88%AD-2/
- ^ https://www.bbc.com/amharic/articles/cer93xdmd18o
- ^ https://yetenaweg.com/%E1%8B%A8%E1%8C%A1%E1%89%B5-%E1%8A%AB%E1%8A%95%E1%88%B0%E1%88%AD-2/
- ^ "Archive copy". Archived from the original on 2023-09-09. በ2023-09-09 የተወሰደ.