የጫካው አምላክ ራስ

ከውክፔዲያ

'የጫካው አምላክ ራስ ' የተባለው የ ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ የመጀመሪያ ስራው ነው። ይህን ቅርጽ የሰራው እድሜው 13 እያለ ነበር። ይህ ቅርጽ በጥንቃቄ አስመስለው የቀረጹት ነው። ዋናው የማይክል አንጄሎ ቅርጽ ሐውልት የደረሰበት አይታወቅም ጠፍቷል።

ታሪኩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

Replica of "Michelangelo as a Youth Carving the Face of a Faun". The original stay in Casa Buonarroti

ሎሬንዞ ዘ ማግኒፊኮ የሳን ማርኮ አትክልት ስፍራ ሲጎበኝ ይህንን ቅርጽ ያያል በጣምም ይገረማል። ነገር ግን የቅርጹ እድሜ እና ጥርሶቹ አብረው አይሄዱም በዚህ እድሜ ያለ ሰው እንዲህ ያለ ሙሉ ጥርስ አይኖረውም ብሎ አስተያየት ሰጠ። ማይክል አንጄሎም ይህን እንደስማ ወዲያውኑ አንዱን ጥርስ ሸረፈው እና ሌሎቹንም አሮጌ እንዲመስሉ አደረጋቸው። ሎሬንዞ ጉብኙቱን ጨርሶ ሊመለስ ሲል በድጋሚ ቅርጹን ቢመለከተው ልክ እሱ እንደተናገረው አድርጎት በማየቱ በጣም ተገረመ። ከዚያም ለማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ ደጋፊው ሆነ። ቅርጹ የት እንደደረሰ አይታወቅም ጠፍቷል [1] [2]

ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • Artists Life — Michaelengelo, page 14,15 — Enrica Crispino, 2001, Giunti Editore.
  • The Life of Michelangelo Buonarroti, page 23 — John Addington Symonds, BiblioBazaar.


ማመሳከሪያዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ወደ ውጭ የሚያገናኙ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Artists Life — Michaelengelo, page 9 — Enrica Crispino.
  2. ^ Lorenzo the Magnificent and young Michelangelo.