የፍሎሬንታይን ሐዘን (Michelangelo)
የፍሎሬንቲን ሐዘን ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ከመስቀል እንደወረደ ሐዘናቸውን ለማሳየት የተቀረጸ ሐውልት ነው። ይህ ሐውልት የተቀረጸው ከ እምነ በረድ ነው። ሐውልቱ የተቀረጸው በ እንደገና መወለድ ቀራጭ ማይክል አንጄሎ ቡናሮቲ ነው። ማይክል አንጄሎ በዚህ ሐውልት ላይ ከ1547 እስከ 1553 ድረስ ስርቶበታል። በሐውልቱ ላይ አራት ሰዎች ይታያሉ። ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱ ክርስቶስ ሞቶ ከመስቀል ላይ ሲያወርዱት ኒቆዲሞስ ( ወይም ዮሴፍ የአሪማቴያ) ማርያም መቅደላዊት እና እናቱ እመቤቴ ማርያም ናቸው። ይህ ሐውልት አሁን የሚገኘው በሙሶ ዴላ ኦፕራ ዴል ዲዮሞ በ ፍሎሬንስ ነው። ማይክል አንጄሎ በመጨረሻ ላይ የቀረጻቸው ሁለት ሐውልቶች (ወይም ሶስት የፓሌስትሪና ሐዘን ጨምሮ) ናቸው። ቫሳሪ እንደሚለው ማይክል አንጄሎ የፍሎሬንስን ሐዘን ሐውልት የሰራው ለራሱ መቃብር ማጌጫ ነበር ለሳንታ ማሪያ ማጆሬ ሮም። ነገር ግን ሐውልቱን በመዶሻ ከሰበረው በኋላ ሰራተኛው ለነበረው አንቶኒዮ ሰጠው። ሰራተኛውም ለሌላ ሰው ሸጠው። አዲሱ ባለቤትም የማይክል አንጄሎን ስራ ይከታተል የነበረ ቲቤርዮ ካልሳጂኒ በሚባል ሐውልት ጠራቢ ስራውን አስጨረሰው። የኒቆዲሞስ ፊት ነጠላ የተከናነበው የማይክል አንጄሎ የራሱ መልክ ነው። በግራ በኩል የምትታየውንም ሴት የጨረሰው ቲቤሪዮ ካልሳጂኒ ነው። ቲቤሪዮ ካልሳጂኒ ይህን ስራ ያገኘው ማይክል አንጄሎ ለስምንት አመት ሐውልቱን ቀርጾ በመጨረሻ ላይ በእምነ በረዱ ላይ ቀድሞ ያላየው ችግር በማየቱ ነው ተናዶ በመዶሻው የመታው እና የተወው።