Jump to content

የፕላቶ ሪፐብሊክ

ከውክፔዲያ

የፕላቶ ሪፐብሊክ በፈላስፋው ፕላቶ ፣ በ390 ዓ.ዓ. የተጻፈ የፍልስፍና መጽሐፍ ሲሆን የሚያተኩረውም የፍትሕን ጽንሰ ሐሳብ በመተርጎምና የ ፍትሐዊ አገር እና ፍትሐዊ ሰው ባህሪዮች ምን ይመስላሉ የሚለውን ጥያቄ በመመለስ ነው።

በዚህ ታዋቂ መጽሐፍ ውስጥ ፕላቶ ሁለት ጥያቄዎችን ያነሳል፣ እነርሱም «ሰዎች ለምን ሰናይ (ጥሩ) ነገር መስራት አለባቸው?» የሚልና « ሰዎች ዕኩይ (መጥፎ) ነገርን ቢሰሩ ሽልማት ያገኙበታል ወይ?» የሚሉ ናቸው። ፕላቶ ሲመልስ፣ ሰዎች መጥፎ ነገርን መስራት የለባቸውም ምክንያቱም መጥፎ ነገር በሰሩ ቁጥር ደስተኛ የመሆናቼው መጠን ይቀንሳል። በተቃራኒው ጥሩ የሚሰሩ ሰዎች ደስተኛ ይሆናሉ።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዕኩይ ሰዎች የአንድ ማህብረሰብ ባለስልጣኖች በሆኑ ጊዜ ያ ህብረተሰብ ደስተኛ እንዳይሆን ያደርጋል። በፕላቶ አስተያየት፣ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ሰናይ ምግባርን ሊከውኑ የሚችሉ ፈላስፎች ናቸው። ስለሆነም ደስተኛ ለመሆን ይሚፈልግ ህብረተሰብ ባለስልጣኖቹ ፈላስፎች መሆን አለባቸው ይላል። ፈላስፋ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ደስተኛ ለመሆን ሲሉ፣ በፈቃዳቸው ለፈላስፎች መገዛት አለባቸው። ሆኖም፣ ፈላስፋ ነገሥታቱ፣ በዕኩይ ተግባር ላይ እንዳይሰማሩ፣ ሃብት ከማካበት እና በፍቅር ውስጥ ከመጠመድ እንዲርቁ የፕላቶ ሪፐብሊክ ይመክራል።

መጽሐፉ የተለያዩ የመንግስት አይነቶችን በዲያሌክቲክ በማዎዳደር ከሁሉ የበለጠውን (የተሻለውን) የመንግስት አይነት ለማዎቅ ይሞክር እንጂ በውስጡ እጅግ ሰፊ የሆኑ መሰረታዊ የሥነ ምግባር ጥያቄዎችንና ሌሎች የፍልስፍና ጥያቄዎችን በማንሳት ይታዎቃል።


ሪፕብሊክ በታም የታወቀ የ ፕላቶ ስራ ነው፤፤