ያልተገናኝቶ ገበያ

ከውክፔዲያ

ያለተገናኝቶ ገብያ - ይህ እንግዲህ ባለተያያዙ እውነታወች ላይ ተነሰቶ ስህተት ውሳኔ ላይ መድረስ ማለት ነው ።

1. adhominem እሱኮ ፦

Quote:

ምሳሌ ፦ አበበ ፦ መንገዶች እየተጣበቡ ስለሆነ ሌሎች መንግዶች መሰራት አለባቸው ።
መሰረት ፦ አንተኮ ታክስ እንኳ አልከፈልክም ፣ ስለመንገድ እና ስለ መንግስት ስራ አታውቅም።

እዚህ ላይ፣ መሰረት የሰራችው ስራ adhominem/እሱኮ ይባላል ምክንያቱም አበበ ያነሳውን ጥሩ ነጥብ ከመወያየት ይልቅ ከነጥቡ ጋር ጭራሽ ግንኙነት የሌለ ነገር አንስታ ውይይቱን ዘጋች።

2. appeal to force/ ዋ !

Quote:

ምሳሌ፦ አበበ ፦ መቸ ነው የሀገራችን ህዝብ ከርሀብ የሚዎጣው ?
ማሞ ፦ አሜሪካ ገብተህ ዝም ብለህ ትዘባርቃለህ ።

ማሞ እንግዲህ ለማለት የፈለገው አሜሪካ ባትገባ ኑሮ ይህን ነጥብ አታነሳም ነበር ። የማያነሳበት ምክንያት ፤ ምግብ ስለተትረፈረፍ ሳይሆን ፤ ይህን ነጥብ ቢያነሳ ሚደርስበት ነገር ስላለ ነው ። ይህ ዋ ! የሚባለው ምክነት ነው ።

3.red herring/ሸወዳ

Quote:

አበበ ፦ ትላንትና ባክሽ የትራፊክ ትኬት አገኘሁ
መሰረት ፦ እንዳትከፍል ! ስንት ሰው ገዳይ ወንጀለኛ እያለ አንት እምትቀጣበት ምንም ምክንያት የለም።

ይህ እንግዲህ ያልተገናኝቶ-ገብያ ዋና መሰረት ነው። አንድ ሰው የሚናገረው ነጥብ ደስ ሳይለን ሲቀር ፣ ሌላ የማይገኛኝ ነገር አንስተን በመሸወድ ሀሳቡን እንዳይጨርስ ስናደርግ ሽወዳ red herring ይባላል ።

Quote: ሌላ ምሳሌ ፦ እናት ለአስተማሪ ፦ ልጀ ፈተና ላይ ኮርጃለች ብለህ ታምን ይሆናል ፣ ነገር ግን ይችን ትንሽ ምስኪን ልጅ እንደገና ፈተና እንድትወስድ ስታደርግ ለህሊናህ አይከብደህም