ያንዲ

ከውክፔዲያ

ያንዲ (ቻይንኛ፦ 炎帝 «የነበልባል ንጉሥ») በቻይና ልማዳዊ ታሪክ መሠረት በሸንኖንግ ነገድ የተጠቀመ ማዕረግ ነበር። አንዳንዴ ሸንኖንግ እራሱ መጀመርያው ያንዲ ይቆጠራል። በዘመናዊ የቻይና ሊቃውንት አስተሳሰብ የያንዲዎች መኖርያ «የበግ ራስ ተራራ» በጋውፒንግ አካባቢ ነበረ።

ከጅያንግ ሽዕንየን ወይም ሸንግኖንግ በኋላ ለ500 አመት ያህል የነገሡት ያንዲዎች በስማቸው ሊንኲ፣ ቸንግ፣ ሚንግ፣ ዥዕ፣ ከ፣ አይ፣ እና ዩዋንግ ናቸው።

ቬትናም አፈ ታሪክ ደግሞ ያንዲ ሚንግ የሎክ ዱክ አባት ነበረ፤ ሎክ ዱክም የ«ሢኽ ቊ» አገር መጀመርያ ንጉሥ («ኪኝ ዲውንጝ ቪውንጝ») ሲሆን በአሁኑ ስሜናዊ ቬትናም መጀመርያውን መንግሥት እንደ መሠረተ ይታመናል።

መጨረሻው ያንዲ ዩዋንግ በባንጯን ውግያ ሞተ፤ ኋንግ ዲ (ቢጫው ንጉሥ) በባንጯን ውግያ (2350 ዓክልበ. ግድም) አሸነፈው። ከዚያ የያንዲ እና የኋንግዲ ነገዶች ተዋሔዱ፣ አንድላይ የኋሥያ ወገን (የቻይና ሕዝብ አባቶች) ሆኑ።