ደረጀ ከበደ

ከውክፔዲያ

ደረጀ ከበደ እውቅ የክርስቲያን ዘማሪ፡ የዘመራቸው መዝሙሮች አብዛኛዎቹ ከሕይወቱ ገጠመኝ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ልዩ ያረገዋል ደረጀ ከበደ የመጀመሪያ ቋንቋው አማርኛ ቢሆንም በኦሮምኛም ዘምሮአል ። ደረጀ በተለይ በውብ ድምጸ ቅላጤው ሲዘምር የሰሚውን ጆሮና ልብ ያነቃቃል። ዝማሬዎቹ የአብዛኞችን ህይወት ለውጠዋል፥ አፅናንተዋል፥ አንፀዋል የክህደት ትምህርቶችን ገስፀዋል በኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት አማኞች ዘንድ በመንግስታት ለተጎዱ ህዝቦች መብት መቆም(injustice) መቃወም የሚያስገፋና መጥፎ ስሞችን የሚያሰጥ ሲሆን ዶ/ደረጀ ከበደ ግን በዝማሬዎቹም በዩትዩብ የምስል ቪዲዮ ኢሰብዐዊነትን ማጋለጡ ለየት ከማድረጉም በልይ ከብዙ ታዋቂ የፕሮቴስታንት አባቶች ጋርም ያመሳስለዋል። ዶ/ር ደረጀ ከበደ የመጀመሪያ ዲግሪውን በአግሮ ኢኮኖሚክስ - በክርስቲያን ትምርህት የማስተርስ ዲግሪ -በ አዲክሽን ስተዲስ የማስተርስ ዲግሪ እና በሄልዝ ሳይንስ በዶክትሬት ተመርቆ እየሠራ ይገኛል።