Jump to content

ደርቆ ተንጣጣ

ከውክፔዲያ

ደርቆ ተንጣጣ

(19) አንድ ሰሞን አለቃ በጣም ቆንጆ ልጅ ያገባሉ። ከዚያም ያው እንደ ባህል ወጉ ልጂቱ እሳቸው ጋ ልታድር ቤታቸው ትሄዳለች። እናም ቀኑ ተገባዶ ማታ ላይ አለቃ ቆጥ ላይ ወጥተው ሲጠብቋት እሷ ማታ ወደ ቤተሰቦቿ ከድታ ልትሮጥ ከቤት ስትወጣ ውጪው እንደአጋጣሚ ዝናባማ ስለነበር አድልጧት ትወድቅና ተመልሳ ቤት ትገባለች። ቤት ገብታም ምድጃ ዙሪያ ተቀምጣ ልብሷን ስታደርቅ ሳት ይላትና ጡጥ ታደርጋለች። ይህን የሰሙት አለቃ «አንቺ አትተኝም?» ይሏታል። እሷም «እስኪ ይቆዩ ልብሴ ምጥጥ ምጥጥ ይበልልኝ» ትላለች። እሳቸውም እሺ ብለም ዝም ሲሉ ልጂቱ አሁንም ደግማ ዛጥ ታደርጋለች።በሁኔታው የተቆጡት አለቃ በስጨት ብለው «አንቺ አትተኝም?» ሲሏት። እሷ «እስኪ ይቆዩ...ልብሴ ይድረቅ ትላለች።» ከዚያም አለቃ ቀጥለው «ኧረ ...ኤዲያ ...ልብስሽ ደርቆማ እየተንጣጣ» ብለው ባሽሙር ጠቅ አረጓት ይባላል።