ደሳለው ጥላሁን መንግስቱ- Dessalew Tilahun Mengistu

ከውክፔዲያ

ደሳለው ጥላሁን መንግስቱ- Dessalew Tilahun Mengistu

የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸው ሰዎች ጠቁሙን ፤ እርስዎም ታሪኬ መሰነድ አለበት ካሉ ይላኩልን፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪክዎን እናወጣለን፡፡ በ tewedajemedia@gmail.com ግለ-ታሪክዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ7 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ሙያቸውን በመደገፍ የራሳቸውን አሻራ ያኖሩ ሰዎች ታሪካቸው ይዘከራል፡፡ በሚድያ ዘርፍ ባለፉት 10 አመታት የራሳቸውን አሻራ ካኖሩት መካከል በተለይ በዜና ፤ በወቅታዊ ውይይትና በዶክመንተሪ ከሚነሱት መሀል ደሳለው ጥላሁን መንግስቱ ይጠቀሳል፡፡

   ትውልድ -ልጅነት -ትምህርት  

ደሳለው ጥላሁን በድሮው ቡሬ ወረዳ በአሁኑ አደረጃጀት አዊ ዞን ጓጉሳ ወረዳ ስር በምትገኘው አዲስ አለም በምትባል የገጠር ከተማ መስከረም 21 ቀን 1976 ዓ.ም ከአባቱ አቶ ጥላሁን መንግስቱ እና ከእናቱ ከወ/ሮ ወርቅነሽ ካሴ ተወለደ፡፡

ከአራት ወንድሞቹ መካከል 2ኛ ልጅ ነበር፡፡ አባቱ አቶ ጥላሁን መንግስቱ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የግሬደር ኦፕሬተርነትን ጨምሮ በተለያዩ ሙያዎች ሰርተዋል፡፡ እናቱ ወ/ሮ ወርቅነሽ ካሴ የቤት እመቤት ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ባለትዳርና የሁለት ሴትና የአንድ ወንድ በድምሩ የሶስት ልጆች አባት ነው፡፡ደሳለው፡፡

በትውልድ ቦታው አዲስ አለም እስከ ሰባት አመቱ ከቆየ በኋላ ከወላጆቹ ጋር ወደ ቡሬ ከተማ በመምጣት ኑሮን ጀመረ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በቡሬ እድገት በህብረት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን ትምህርቴን ደግሞ በቡሬ አቲከም አንደኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል በቡሬ ሽኩዳድ ሁለተኛ ድረጃ ትምህር ቤት እንዲሁም የመሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኘው የዳሞት ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡

     ዩኒቨርሲቲ  

በ1996 ዓ.ም የተሰጠውን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና በማለፍና በጎንደር ዩኒቨርስቲ በመመደብ ለሶስት ዓመት የተከታተለውን የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነጽሑፍ ትምህርት በማጠናቀቅ በ1999 ዓ.ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል፡፡ በ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ባመቻቸለት የትምህርት እድል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን የትምህርት መርሃ ግብር በመከታተል በጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን የትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ MA ትምህርቱን በ2010 ዓ.ም አጠናቅቆአል፡፡ በዚሁ የትምህርት ቆይታውም Consensus on the Grand Ethiopian Renaissance Dam(GERD); Media Coverage on the Reporter(Amharic) and Addis Zemen በሚል ርዕስ የምርምር ስራውን አከናውኖአል፡ በአሁኑ ሰዓትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኤክስቴንሽን የትምህርት መርሃ ግብር በ International Relation and Diplomacy የትምህር ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ MA ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል፡ በቋንቋ እና በጋዜጠኝነት ላይ ትኩረት ያደረጉ አጫጭር ስልጠናዎችን በውጭ ሀገራት በግብጽ፣በህንድና በፖላንድ ወስዷል፡፡

የሚድያ ሰው የመሆን ዝንባሌ  

የጋዜጠኝነት ሙያ በደሳለው ውስጥ የተጸነሰው በልጅነቱ ነው፡፡ ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ በቋንቋ እና ስነጽሑፍ ክበባት ከመሳተፍ ባለፈ በሚኒ ሚዲያ አማካኝነት የጋዜጠኝነት ሙያን ይለማመድ ነበር፡፡ በተለይ በቡሬ ዕድገት በህብረት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘወትር በጠዋት ሰልፍ ላይ ለተማሪዎችና ለመምህራን እንዲሁም በዓመታዊ የወላጆች ቀን በዓላት ላይ ያቀርባቸው የነበሩ ዝግጅቶችና ይሰጡት የነበሩት የሞራል ማበረታቻዎች ከመደበኛው ትምህርቱ ጎን ለጎን የጋዜጠኝነት ሙያውን እና የስነጽሑፍ ተሰጥኦውን እያጎለበተ እንዲሄድ እድል ፈጥሮለታል፡ በዚሁ የትምህርት ቆይታው በ1987 ዓ.ም በቡሬ ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል በተካሄደው የስነ-ጽሁፍ ውድድር 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ በመውጣት ማሸነፉ የዚሁ ማሳያ ነው፡፡ በቡሬ 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበረው የትምህርት ቆይታም ይሄንኑ ልምምዱን በማጠናከር በ1990 የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት /የገና)ን በዓል በቡሬ ከተማ ቡሬ የለስላሳ መጠቶች ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ባከበረበት ልዩ ዝግጅት ላይ በእንግድነት ተጋብዞ በዕለቱ ያዘጋጀውን ዜና እና ግጥም ለታዳሚዎች አቅርቦአል፡፡ በመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ፊትም በልጅነቱ የተጸነሰውን የጋዜጠኝነት ፍላጎት እና የወደ ፊት ምኞቱን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሰጥቶአል፡፡ ይሄም በወቅቱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በመተላለፉ ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖት ነበር፡፡ ደሳለው በልጅነቱ ለስነጽሁፍ ሲል ያደረግ የነበረውን ሙከራና ይህ ጥረቱ ወደየት እንዳደረሰው እንዲህ ሲል ይገልጸዋል ‹‹…………..በዳሞት ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ምህርት ቤትበነበረኝ የትምህርት ቆይታዬም ይሄንኑ የጋዜጠኝነትና የስነጽሑፍ ፍላጎቴን ይብልጡን አጠናክሬ ተጉዣለሁ፡፡በፍኖተሰላም የዳሞት ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርት ቤት በነበረኝ የትምህርት ጊዜም የትምህርት ቤቱ የሚኒ ሚዲያ ክበብ ኃላፊም ጭምር በመሆን ሰርቻለሁ፡፡ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ቆይታዬም ከመደበኛው ትምህርቴ በተጓዳይ በዩኒቨርስቲው የሚኒ ሚዲያ ክበብ እና በማሕበረ ቅዱሳን ጎንደር ቀርንጫፍ የማራኪ ግቢ ጉባኤ በመሳተፍ በልጅነቴ የተጸነሰውን የልጅነት የጋዜጠኝነት ህልሜን የበለጠ ማጎልበት ችያለሁ፡፡ በልጅነት የጋዜጠኝነት ህልሜ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴና እና ጋዜጠኛ ብርቱካን ሐረገወይን አብነቶቼ ነበሩ፡፡ "ማንን መሆን ትፈልጋለህ?" ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ መልሴ የነበረው አለምነህ ዋሴንና እና ብርቱካን ሐረገወይንን የሚል ነበር፡፡

    የስራ አለም 

በያኔ ስያሜው የማስታወቂያ ሚኒስቴርና በኋላ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ተብሎ ይጠራ በነበረው እና ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በፈረሰው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ህዳር 19 2000 ዓ.ም ጀምሮ በመቀጠር የሁነት ፈጠራና ፕሮሞሽን በሚባል የስራ ክፍል ውስጥ በወቅቱ በየሳምንቱ ዓርብ የመንግስት የአቋም መግለጫ ተብሎ የሚቀርበው መልዕክት ቀረጻ እና የኤግዚብሽን ስራዎች ዝግጅት ላይ ለአንድ ዓመት ያህል ሰርቻለሁ፡፡ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በወቅቱ በመንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ስር "የዜናና ፕሮግራም ፕሮዳክሽን ዳይሬክቶሬት" በሚል እንደ አንድ ዳይሬክቶሬት ተዋቅሮ ይሰራ በነበረው እና በ1996 ዓ.ም በአዋጅ ወደ ቀደመ ህልውናው በተመለሰው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በመዛወር ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና አዘጋጅ የጋዜጠኝነት የሙያ ደረጃዎች እየሰራሁ እገኛለሁ፡፡

     ኢዜአ  

በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ባለኝ ከ12 ዓመት በላይ ስራ ቆይታም አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አከባባቢዎች በመዘዋወር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ይዘት ያላቸውን ዜናዎች፣ፕሮግራሞች ዘጋቢ ፊልሞች እንዲሁም በትልልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን በማዘጋጀት ስራዎቼ የክልል ሚዲያና የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተላልፈዋል፡፡ በዜና ኤዲተርነትም አገልግያለሁ፡፡›› በማለት ገልጾት ነበር፡፡ በቅርብ ጊዜያት በኢትዮጵ አንድነትና ሰላም፣ በታላቁ የህዳሴው ግድብ፣የጣና ሐይቅን ከእንቦጭ አረም ለመከላከል ምን እናድርግ በሚል ያዘጋጃቸውና በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተላለፉ ስራዎቹ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

       ሌሎች 

ከአንድ ወር ያልበለጠ ቆይታ ቢኖረውም መቀመጫውን በአሜሪካን ሀገር ባደረገው የመረጃ ቴሌቭዥን ወቅታዊ ዝግጅት ላይ በምክትል ዋና አዘጋጅነት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን አዘጋጅቷል፡፡ በትምህርት ቆይታው በ1991 እና በ1995 ዓ.ም የዘጠነኛ እና የ11 ክፍል ተማሪ ሳለ የልጅነት ህልሙን የሚያደናቅፉ ከባድ የሆኑ ሁለት የጤና እክሎች ገጥመውት የነበረ ቢሆንም በህክምና እና በጸበል እርዳታ ከችግሮች በመውጣት ትምህርቱን ከማጠናቀቅ ባለፈ ጋዜጠኛ የመሆን የልጅነት ህልሙን አሳክቷል፡፡ ደሳለሁ ታሪኩን እንዲህ በማለት ቀጠለ.. ‹‹………ኢ¬-ፍትሃዊ አሰራርና በደልን አጥብቄ እቃወማለሁ፡፡ ለአመንኩበት ነገር እስከ ህይወት መስዋዕትነትም ቢሆን ለመክፈልና ለመጋፈጥ ሁሌም ዝግጁ ነኝ፡፡ ስህተትን አይቼ አላልፍም ፊት ለፊት እጋፈጣለሁ፡፡ ይሄ ባህሪዬ ብዙዎችን አያስደስትም፡፡ ለእኔም በስራ ዓለም በቆየሁባቸው አመታት ብዙ ዋጋ አስከፍሎኛል፡፡በ2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፊት ለፊት በመጋፈጤ በወቅቱ ተቋሙን ተቋሙን ይመሩ በነበሩ ግለሰብ ማን አለብኝነት ከስራ ገበታዬ እስከ መባረር ደርሻለሁ፡፡ የተፈጸመብኝ በደል ፍትሃዊ አለመሆኑን የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች አማካኝነት በመሞገትና ህብረተሰቡም ሆነ የሚመለከተው አካል በወቅቱ እኔ ላይ የተፈጸመውን በደል እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ከሰባት ወራት ተስፋ አስቆራጭ ትግል በኋላ በግፍ የተነጠቅሁትን የጋዜጠኝነት ሙያዬን በፍርድ ቤት በማስመለስ ወደ ስራ ገበታዬ ተመልሻለሁ፡፡ ይህ ጊዜ በጋዜጠኝነት የሰራ ቆይታዬ ለእኔም ሆነ ለቤተሰቤ ከባዱ ጊዜ የነበረ ቢሆንም የእውነት ዋጋ መቼም ቢሆን አይቀልምና በስኬት መወጣት ችያለሁ፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ ከመደበኛው የጋዜጠኝነት ሙያው ጎን ለጎን ለማህበራዊ ሚዲያ ጓደኞቹ የሚያገኛቸውን ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ያካፍላል፡፡ ይሄም ፍጹም ደስታና እርካታን ያጎናጽፈዋል፡፡›› https://www.facebook.com/dessalewt https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/2740865909489204/ https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/2824430747799386/ https://www.facebook.com/ethiopianewsagency/videos/2615168025397805/