ደብረ አቡነ ሙሴ

ከውክፔዲያ

ደብረ አቡነ ሙሴ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ከአለት የተፈለፈ ቤተ ክርስቲያን ነው።

ከአለት የተፈለፈለ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
የዶጋ አቡነ ሙሴ
  1. ይነበብ ይነበብ ይነበብ #በፃዲቁ ስም #ሼርም ያድርጉ።

✝ብጹዓዊ አቡነ #ሙሴ ✝

“የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው “ ምሳ 10፣7

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በቤተክርስቲያናችን መስከረም 4 በዓለ እረፍታቸው የሚከበረው አቡነ ተክለሐይማኖት ፣አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ፣ አቡነ አሮን ፣አቡነ መብዓ ጽዮን ፣ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስና ቅድስት አርሴማን በቆብ የወለዱት ብጹዕ አቡነ ሙሴ ማን ናቸው? ምንስ ተጋድሎ አደረጉ? ምን ምን ቃል ኪዳን ተሰጣቸው? እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እንመለከታለን፡፡

ብጹዕ አባታቸችን በአባታቸው የእመቤታችን ጠባቂ የሆነው የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ የልጅ ልጅ ሲሆኑ በእናታቸው በኩል ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በቃና ዘገሊላ ሰርግ የተገኙበት የዶኪማስ የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ 👉🏾 የአባታቸው ስም #ቅዱስ ዮስጦስ ሲባል የእናታቸው ስም ቅድስት #ጵርስቅላ ይባላሉ፡፡ ቅዱስ ዮስጦስ የዳዊት ወገን ሲሆኑ ቅድስት ጵርስቅላ /ሶልያና ማርያም/የካህኑ የአሮን ወገን ነች፡፡ ሁለቱም ልጅ ሳይወልዱ መካን ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ ሊቀ መልአክት ቅዱስ ፋኑኤል ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ለቅድስት ጵርስቅላ ልጅ እንደምትወልድ አብስሯት በሰውነቷ ላይ በስትንፋሱ እፍ ብሎ ቀደሳት በሊቀ መልዕክት ቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ታህሳሥ 8 አቡነ ሙሴ ተወለዱ፡፡ በልደታቸውም ቀን ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተገኝተው ስሙን ሙሴ ተብሎ እንዲጠራ ወላጆቻቸውን አዘዟቸው ፡፡በብሉይ ዘመን ነቢዩ ሙሴ ህዝብ እስራኤልን እየመራ ከባርነት ነጻ እንዳወጣ በሀዲስ ያሉትን ደግሞ መርቶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ህዝቡን ይመልሳል፡፡በዚህች ቀን ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸን ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ በ40ኛው ቀን ሊቀ መልአክት ቅዱስ ዑራኤል ለሐዋሪያው ቅዱስ ያዕቆብ ተገልጾ በቤተክርስቲያን አቡነ ሙሴን ክርስትና እንዲያነሳ አዘዘው፡፡ 👉🏾አቡነ ሙሴም የሥላሴን ልጅነት ጥር 18 አገኙ በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጸሙ፡፡ በሶስት አመታቸው ወላጆቻቸውን በተሳሉት ስዕለት መሰረት ለቤተክርስቲያን ሰጧቸው ፡፡ ምግባቸውን ቅዱሳን መልአክት ቅዱስ ፋኑኤልና ቅዱስ ዮናኤል ህብስተ ሰማያዊ እያመጡ ይመግቧቸው ነበር፡፡ምድራዊ ምግብና መጠጥ ፈጽሞ አልተመገቡም፡፡ 👉🏾 እመቤታችን ድንግል ማርያም በቅዱስ ዮሐንስ ቤት ሳለች አባታችን በህጻን እድሜአቸው ወደ ወንገሌዊው ቤት በመሄድ እናታችንን አገልግለዋል ብዙ ሚስጢርንም ተምረዋል፡፡ 👉🏾ሰባት ዓመት ከሆናቸው ጀምሮ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማያት ጋር የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን መንበር ያጥኑ ነበር በድንግልናቸው በንጽህናቸው እንደ ሱራፌል ክንፍ ተሰጥቷቸዋል አቡነ ዘበሰማያት በጀመሩ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተውላቸው አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ እና ቅዱሳኑን በግልጽ ያያሉ፡፡ስግደት እጅግ ከማብዛታቸው የተነሳ እንባቸው በደረታቸው ወርዶ መሬት ላይ ይንጠባጠብ ነበር፡፡

👉🏾ጌታችን በተሰቀለ አስራ ሶስት አመት በሆናቸው ጊዜ ጌታችን ከጴጥሮስ ጋር ቅዳሴ ገብቶ ለደቀመዛሙርቱ ሁሉ ሲያቀብላቸው አቡነ ሙሴንም ከሀዋሪያቱ ጋር አብረው ተቀብለዋል፡፡ 👉🏾ከእለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በግብጽ እና በእስራኤል መካከል እያገለገሉ ጣዖትን ለማሳፈር ወደ መቅዶኒያ በመሄድ ጣዖት የሚያመልከውን ንጉስ ገሰጹት ንጉሱም ተቆጥቶ አጥንታቸው እስኪታይ ድረስ ደብድቦ በብረት አልጋ ላይ በማስተኛት እሳት አነደደባቸው ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ግን እሳቱን እንደውሃ አቀዝቅዘው ዳሰው ፈውሰዋቸዋል በማግስቱም ወደ ፍርድ አደባባይ ሲወስዷቸው ምንም እዳልሆኑ ንጉስ በማየቱ በንዴት ሰውነታቸውን በሰይፍ አስቆራረጠው ከአቡነ ሙሴም ሰውነት ደው ፣ ውሃ፣ ወተትና ማር ወጣ ጌታችንም ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ አዳናቸው

👉🏾እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጣቸው በስምህ የተማጸነውን መልካም ነገርን አደርግለታለሁ አላቸው፡፡ 👉🏾በግብጽ ግብጻውያን በአቡነ ሙሴ ቅድስና በመማረካቸው እንዲሁም የዳዊት ወገን በመሆናቸው ንግስና ይገባቸዋል በማለት አንስጣስዮስ ቴዎዶስዮስ በሚል ስም አቡነ ሙሴ ንግስና ተሾሙ፡፡

👉🏾ብጹዕ አቡነ ሙሴና ኢትዮጲያ ብጹዕ አባታችን በአብርሃ ዘመነ መንግስት የኢትዮጲያ የመጀመሪያው ከሳቴ ብርሃን አቡነ ሰላማ በማረፋቸው ሁለቱ ቅዱሳን ነገስታት ከ318 ሊቃውንት አንዱ ወደ ሆነው ወደ መንበረ ማርቆስ ላይ ሆኖ ክርስትናን ከሚያጸናው ከአቡነ አትናቴዎስ ዘንድ ጳጳስ እንዲልኩላቸው ከእጅ መንሻ ጋር ወደ ግብጽ ላኩ፡፡ አቡነ አትናቴዎስ ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው አቡነ ሙሴን ለኢትዮጲያ አባት እንዲሆኑ እና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የጀመሩትን እንዲያጸኑ ወደ ነገስታቱ ላካቸው፡፡ስለዚህም ካልዕ ሰላማ ተብለዋል(ድርሳነ ዐራኤል ዘሚያዚያ) ከሶስት ሺህ ልጆቻቸው ጋር ሆነው ብዙ ቅርስ ይዘው አባታችን ወደ ኢትዮጲያ ሲመጡ ምዕመናኑ በደስታ ተቀበሏቸው፡፡ 👉🏾በተጨማሪም በገድለ ቅድስት አርሴማ በሰባተኛው ተአምር እንደተገለጸው ቅድስት አርሴማ ሳትወለድ በስሟ የተሰየመውን ታቦት ወደ ኢትዮጲያ ይዘው መጥተዋል፡፡ 👉🏾ብዙ መጽሐፍትንም ከአረብኛ ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡ 👉🏾ብጹዕ አባታችን በደብረ ምጥማቅ ፣በፍልስጤም ፣በቢታንያ ፣በሆሳዕና ፣በናዝሪት ፣በገሊላ ፣በሊባኖስ ፣በኬብሮን ፣በፋርስ ፣በባበሎን … በአጠቃላይ በመላው ዓለም አስር ሺ (10000) ቤተክርስቲያን በኢትዮጲያ አምስት መቶ (500) አብያተክርስቲያን አንጸዋል፡፡ 👉🏾የቤተክርስቲያህንጻ ግንባታ ስራ ከመጀመራቸው በፊት 40 ቀን ይጾማሉ ሁለቱ መልአክት ቅዱስ ፍርክኤል እና ቅዱስ ፍናኤል ከአባታችን ሳይለዩ እየረዷቸው ቤተ መቅደስን ያንጸሉ፡፡ 👉🏾የዋሻ ቤተመቅደስ ሲሰሩ ድንጋዮች ሳይቀሩ ይታዘዙላቸዋል ከዚህ ጎን ለጎን ታቦት መቅረጽ ፣መስቀል መስራት ፣ንዋያተ ቅድሳት መስራት የሚያከናውኗቸው ተግባራቶች ናቸው፡፡ከሚሰሯቸው ዋሻ መቅደሶች ውስጥ ከፊሉ የሚታይ ህዝበ ክርስቲየን የሚገለገልባቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ የማይታዩና ስውራን እናቶችና አባቶቸ የሚገለገሉባቸው ናቸው፡፡ በእንቁና በእምነበረድ ከሰሯቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ በአራራት ደብር/ከምድር ጥፋ በኃላ የኖህ መርከብ መጀመሪያ ያረፈችበት /በጻድቁ ኖህ ስም ፣አብርሃም አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴን ባስተናገደበት ስፍራ በሥላሴ ስም ፣ በህንድ /የሐዋሪያው ቅዱስ ቶማስ መቃብር ቦታ/በቅዱስ ቶማስ ስም ፣ በአርማንያና በግርበስ /የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስጋውን ተሸክመው አምጥተው በአስቀመጡበት ቦታ/ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ፣ በአስቄጥስ ገዳም /የመጀመሪያው በገዳሙ የተሰራው ቤተክርስቲያን/በአቡነ እንጦስ ስም ፣ በግብጽ ደብረ ምጥማቅ /በድንግል ማሪያም ስም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

👉🏾ካልዕ ሰላማ /አቡነ ሙሴ/በኢትዮጲያ ካነጹት የዋሻ መቅደስ ውስጥ 1. ደብረ ቢዘን መድኃኔዓለም ገዳም - በኤርትራ 2. አዲስ አምባ መድኃኔዓለም ገዳም - ወቄት ወረዳ 3. የጭራ መድኃኔዓለምና ቅድስት አርሴማ ገዳም - ጋሸና ወረዳ /አሁንም የአቡነ ሙሴ ጭራ የሚገኝበት/ 4. ወይንዬ ማርያም -ወልዲያ ሳንቃ 5. ዙር አባ አቡነ አረጋዊ - ጎንደር /ከቤተክርስቲያኑ ውጪ የጻዲቁ ዋሻ ቤተክርስቲያ የሚገኝበት/ 6. ወልደነ ጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ - ጋሻና ወረዳ-ኮን 7. አእማድ ቅድስት ስላሴ ገዳም - መቄት ወረዳ/እንደ አቡነ አሮን መንክራዊ ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማገባው በአቡነ ሙሴ የታነጸው / 8. 👉🏾የዶጋ አቦ አቡነ ሙሴ ገዳም 9. ቁስቋም ማሪያም - ሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ 10ጻዲቁ አቡነ ተክለሃይማኖት - ሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ 11. ቅዱስ ጊዮርጊስ - ዳውንት /ብዙ ሚስጢር ያለበት ስፍራ 12. አርባእቱ እንስሳት - ዳውንት 13. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳም - ዳውንት /አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የእረፍት ቦታ 14. ቅድስት ማርያም - ዳውንት 15. ገዳም ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል - መቄት ፍቅርተ ክርስቶሳ ገዳም 16. የድባ መቅደስ ማርያም አቡነ ሙሴ ገዳም - ሰሜን ወሎ ዳውንት አቡነ ሙሴ በመጨረሻ ያነጹትና የእረፍት ቦታቸው ነው፡፡

✝አቡነ ሙሴና ቅድስት አርሴማ የብጽዕት ቅድስተ አርሴማ ሰባተኛ ተዓምር ይህ ነው በግብጽ ከተማ በእስክንድሪያ ስሙ አንስጣስዮስ የሚባል ቴዎደስዮስ የሚሉት አንድ ንጉሥ ነበር፡፡የጵጵስና ስሙም ይህን ዓለም የናቀና የእግዚአብሔር መንገድ የተከተለ ብጹዓዊ ሙሴ ነው፡፡ ይችውም የምንኩስና ህጉ ናት እርሱ የቅዱሳን ሰማዕታትንና የጻድቃንን አጥንቶች ይሰበስብ የገድላቸውን ዜና ይጽፍ ቤታቸውን ይሰራ ታቦታቸውን ያገባ በየበዓላቸውም ይቀድስ ሁል ጊዜ ታቦቶቻቸውን ይጎበኝ ነበር፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀንም ታቦትን ለማሰናዳትና ሜሮን መቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ሲዳስስ በወርቅ የተለበጠ በላዬ በሮማይስጥና በጽርህ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት አገኘ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰበ፡፡የገድላቸውንም ዜና መረመረ የብጽእት ቅድስት አርሴማን የሞትዋን ዜና አላገኘም ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች የብጽዕት ቅድስት አርሴማን ስራ ያስረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለት እንዲህም አለው ብጹአዊ ሙሴ ሆይ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን ሥራ እነግር ዘንድ ስማ ይቺ ሰማዕት ዛሬ አልተጸነሰችም አልተወለደችም በወርቅ አምድ በህይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ ነብዬ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ፡፡ እርስዋም በኃለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል የሚበዛውም በነጻ አውጪ አገር ኢትዮጲያ ውስጥ ነው አለው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰቢያ መጥራት አትተው ጽላቷም ከአንተ ጋር ይሁን የመቅደሷ ህንጻ በህንጻ ቦታህ ጎን ይኑር ስምህ በተጠራበት የስሟ መታሰቢያ ይጠራ ይህንን ብሎ ያ መልአክ ተሰወረ ወደ ላከውም ተመለሰ እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ✝አቡነ ሙሴና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶሰ ከአንድ ሺ ዘመን የአቡነ ሙሴ ገዳም ምስረታ በኃላ ዳግማዊ ተክለሃማኖት የተባለው አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ተወልዶ ለትምህርት ወደ አቡነ ሙሴ ገዳም በ5 ዓመቱ መጣ አባቱ እስትንፋሰ ክረትስቶስ ከድንጋይ በታነጸች ዋሻ 62 ዓመት አንዲት ልብስ ለብሶ ወደ ኖረው የደብረ ድባ መምህር/አቡነ ሙሴ ገዳም/ ስሙ ኪራኮስ ወደሚባል ጻድቅ ወሰደው፡፡አበምኔቱም ብዙ ጸሎት አድርሶለት የሐዋሪያው የቅዱስ ዮሐንስን መልዕክት ሲያስተምረው በአንዲት ሰዓት አወቃቸው (ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገጽ 6-7) ለሐይቅ እስጢፋኖስ አበምኔት ሶስት ዓመት ካገለገለ በኃላ ምንኩስና ልብስ ለበሰ፡፡የኢትዮጲያ ሊቀ ጳጳሳትና የገዳማት አለቃ የመነኮሳት አባት ከሚሆን ከአባ ሙሴ ህንጻ ደብረ ድባ ተቀበል አለው(ገድለ አቡነ እስትንፋ ክርስቶስ ገጽ 17)አቡነ ሙሴም ቆብና ሥልጣኑን ሲሰጠው ሁሉ ይገዛልሃል እንዳለው ዘመዶቹ በእርሱ ላይ ስላለው ታላቅ ግርማ እጅግ ተደሰቱ (ገድለ አቡነ እስትንፋ ክርስቶስ ገጽ 46) 👉🏾ሌላው የሚደንቀው የአቡነ ሙሴና የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የልደት ቀን ታህሳሥ 8 ነው፡፡

✝አቡነ ሙሴና አቡነ መብአ ጽዮን አቡነ እንጦስ ወልዶ አቡነ መቃርስ ፣ አቡነ መቃርስ ወልዶ አቡነ ሙሴ ፣ አቡነ ሙሴ ወልዶ አቡነ መብዓ ፅዮን አቡነ መብዓ ጽዮን ሲነሳ የመድኃኔዓለም ፍቅር በልባችን ያኖሩ አባት ናቸው አመታዊ ክብረ በዓላቸው ጥቅምት 27 ነው በገድለ አቡነ ሙሴ እንደተገለጸው አቡነ መብዓ ጽዮንን በጸጋ በረከት የወለዱልን አቡነ ሙሴ ናቸው፡፡ለዚህም ከአቡነ መብዓ ጽዮን በፊት መድኃኔዓለምን ለኢትዮጲያውያን የዋሻ ቤተመቅደስ በስሙ በመስራት የሰበኩልን አቡነ ሙሴ ናቸው፡፡ለምሳሌ ደብረ ቢዘን መድኃኔዓለም ኤርትራ ፣አዲስ አምባ ላይ መድኃኔዓለም ከብዙ በጥቂቱ ይገኛሉ/፤፤ ይህ ሁሉ አቡነ መብዓ ፅዮን ሳይወለዱ የታነጹ ናቸው፡፡ 🔅የአቡነ ሙሴ ጸጋ🔅 1. ዘውገ መላዕክት /የመላዕክት ወንድም 12 ክንፍ ያላቸውን በመሆኑ እንደ መልአክት ይራዳሉ

2. አረጋዊ አባት -ከ500 ዓመት በላይ በዚህ ዓለም ኖረው አገልግለዋል

3. ባሕታዊ - ከሰዎች ተለይተው ለወገን በጸሎት ይተጉ ነበር

4. የመነኮሳት አባት - መነኮሳየረትንና መነኮሳትን ወልደዋል ለምሳሌ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ፣አቡነ መብዓ ፅዮን .አቡነ አሮን መንክራዊ ……

5. ጋብቻን የሚቀድሱ - የቃና ዘገሊላ የሙሽሮች ፍሬ ናቸው

6. ሀናፂ መቅደስ - ከቅዱስ ላሊበላ ከ700 ዓመት በፊት ብዙ ዋሻ ቤተመቅደስ አንጸዋል

7. ሊቀ ጳጳስ - በጌታ ሐዋሪያት እጅ ጵጵስናን ተሸመዋል

8. ሀብተ መንግስት - የቅዱስ ዳዊት ወገን በመሆናቸው በመላዕክት እጅ የመንግስት ቅባት ተቀብተው አርባ/40/ ዓመት በግብጽ አስተዳድረዋል

9. ሱራፌል - ከሰባት ዓመታቸው ጀምሮ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በመሆን መንበረ ጸባኦትን አጥነዋል

10. ጥበብ የሚገልጽ - ህጻን ሆነው በፅርሃ ፅዮን ከሀዋሪያት ጋር ስለነበሩ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አድሮባቸዋል ፡፡ 👉🏾አባታችን ብዙ ተጋድሎ ካደረጉ በኃላ አምላካችን ለጻዲቁ እልፍ አእላፋት መላዕክትን አስከትሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው ስምህን የጠራ ዝክርህን ያዘከረ ለቤተክርስቲያንህ መባ የሰጠ ልጆቹን በስምህ የሰየመ ባነጽካቸው ቤተክርስቲያን የተቀበረ እስከ 15 ትውልድ እምርልሃለው ፡፡ ዘወትር ወደ ቤተክርስቲያንህነ የሚጎበኝ አራዊት አይነኩትም ፡፡ ይልቁንም የእረፍትህን ስፍራ የተሳለመ በቦታው የተቀበረ እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እስከ 55 ትውልድ እምርልሃለው ብሎ ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን በመጨረሻ ባነጹት መቅደስ የድባ መቅደስ ማርያም መስከረም 4 ቀን በእለተ እሁድ አረፉ ፡፡ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች፡፡ በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ

🔐ጻድቁ ለምን ስማቸው ብዙ ሳይታወቅ ቆየ❓

✍🏽በአራት ስም ስለሚጠሩ 1⃣የክርስትና ስማቸው ሙሴ ነው 2⃣ የንግስና ስማቸው አንስጣቴዎስ ቴዎዶስዮስ ነው 3⃣የምንኩስና ስማቸው ተክለ ማርያም ሲሆን 4⃣የጵጵስና ስማቸው በኢትዮጲያ ካልዕ ሰላማ /አቡነ ሚናስ/ ተብለው ስለሚጠሩ ነው፡፡

አድራሻ

የመካነ ህይወት የዶጋ አቡነ ሙሴ ደብረ ሲና ማርያም  ገዳም 

ከአዲስ አበባ ላልይበላ መስመር 651 ኪ.ሜ ከደሴ ላሊበላ መስመር 250 ኪ.ሜ ከወልዲያ ላሊበላ መስመር 130 ኪ.ሜ ከባህርዳር ላሊበላ መስመር 194 ኪሜ

ለበለጠ መረጃ 0926212121(0911160306)

{{}}
አገር ኢትዮጵያ
ሌላ ስም {{{ሌላ ስም}}}
ዓይነት ውቅር ቤተክርስቲያን
አካባቢ** ሰሜን ወሎ የዶጋ አቡነ ሙሴ
የቅርስነት ታሪክ
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን 368 በነገስታት አፅብሃ ዘመን 
* የአለበት ቦታ
** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል