ደብረ ወርቅ
Appearance
ደብረ ወርቅ | |
ከፍታ | 2,489 ሜትር |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 13908 |
ደብረ ወርቅ በምስራቅ ጎጃም፣ እናርጅ እናውጋ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙት ሁለት ከተሞች ታላቁ ነው። በከተማው ዳርቻ የሚገኘው የደብረ ወርቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በአካባቢው ዘንድ ታዋቂነትን ያስገኘዋል።
ደብረወርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኘው ፣ ከዚሁ አካባቢ የፈለሱ ተሳላሚዎች ፋዩም፣ግብጽ ውስጥ ዳር አል አብያድ በተሰኘ ገዳም ስማቸውንና የመጡበትን ቦታ በቀለም ስላስመዘገቡ ነው ። ይሄውም በ ሰኔ 8፣ 222 ዓመተ ምህረት ( ሰኔ8፣ 1038 ዓ.ም.) መሆኑ ነው። [1][2] ዓፄ በእደ ማርያም ሕዳር 12፣ 1470 በዚሁ ቦታ በሞት እንዳረፉ ይጠቀሳል [3]።
- ^ Encyclopaedia Aethiopica: He-N, Otto Harrassowitz Verlag GmbH, Wiesbaden Germany (2007) , ገጽ 163
- ^ Wladmir De Bock, Matériaux pour servir à l'archéologie de l'Égypte chrétienne, St-Petersburg, page 54, figure 65
- ^ Problemi attuali di scienza e di cultura: quaderno,Accademia nazionale dei Lincei, Issues 190-192 (1972), ገጽ 550