ዲየጎ ማራዶና

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሙሉ ስሙ ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ሲሆን አርጀንቲናን ለዓለም ዋንጫ ያበቃት ድንቅ የእግር ኳስ ተጫዋች ነው። ማራዶና የትውልድ አገሩን አርጀንቲና ለ1986ቱ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ድል አብቅቷል። በ1990 የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ጣሊያን ላይ ለፍጻሜ ግጥሚያ አድርሷል። በ2010ሩ የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫም የአሰልጣኝንት ሚና ተጫውቷል። ዲዬጎ ማራዶና በ60 ዓመቱ ህይወቱ ያለፈው ከቦነስ አይረስ ከተማ ፈንጠር ብሎ ባለው ቤቱ በልብ ድካም ሕመም ነው።