ዳያሌክቲክ

ከውክፔዲያ
ሄግል

ዳያሌክቲክፍልስፍና ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ያስተሳሰብ አይነት ነው። ይህ ዘዴ በጥንቱ ግሪክ ሲሰራበት ቆይቶ በፈላስፋው ፕላቶ ለፅሁፍ በቅቷል። መሰረቱም፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የተለያዩ አስተያየት ያላቸው ሰወች እርስ በርሳቸው በመነጋገር ለመተማመን ከሚያደርጉት ጥረት የሚነሳ ነው። ይህ ከሬቶሪክ ይለያል፤ ምክንያቱም በሬቶሪክ አንድ ግለሰብ ብቻ ብዙ ጊዜ የወሰደ ንግግር በማድረግ የራሱን ሃሳብ ለሌሎች ማሳመኛነት ሲያቀርብ ስለሆነ ነው።

እንግዲህ በዘመናት ሂደት የተለያዩ አይነት ዲያሌክቲ ዘዴወች ተነስተዋል። ከብዙ በጥቂቱ የማርክስሄግልፕላቶሶቅራጥስና የህንዶቹን ፍልስፍናወች ይጠቀልላል።

መሪ ሃሳቦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዲያሌክቲክ አስተሳሰብ እንዲሰራ አስፈላጊ የሆኑ መሪ ሃሳቦች (ዓለምን የመመልከቻ ዘዴወች ወይም ርዕዮተ አለሞች)፣ ከነዚህም 4ቱ ወሳኝ አስተሳሰቦች እኒህ ናቸው፦

1)ሁሉም ነገር አላፊና የተወሰነ ነው፣ የሚኖረውም በጊዜ ወሰን ውስጥ ነው
2)ሁሉም ነገር ከተጻራሪ ሃይሎች ወይም ጎኖች ነው የተሰራው
3)ቀስ በቀስ የሚመጣ ለውጥ በስተመጨረሻ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል በዚህም አንደኛው ሃይል/ጎን ሌላኛውን ያሸንፋልና። (የመጠን ለውጥ የጥራት ለውጥ ያመጣል)
4)ለውጥ ክብ እየሰራ ሳይሆን የሚንቀሳቀሰው (መለት ለውጥ ወደ ነበርንበት ሳይሆን የሚመልሰን) እንደ ስፓይራል መንገደ እየከፈተ እና እያደገ ነው ሚሄደው

የጥንቱ ዲያሌክቲክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የመካከለኛው ዘመን ዲያለክቲክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሄግል ዲያሌክቲክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ ታዋቂው ዘዴ ሲሆን በ3 ደረጃወች ተከፍሎ ይቀርባል። ይኸውም በመጀመሪያ ደረጃ ተናጋሪ ቴሲስ ወይም እርሱ እውነት ነው ብሎ ያሰበውን አስተያየት ያቀርባል። በዚህ ጊዜ ተቃውሞ አንታይ ቴሲስን ያስነሳል። በስተመጨረሻ ይህ የሚያሰነሳው ቅራኔ በ ሲንቴሲስ ( ውህደት ) ይረግባል። በዚህ መንገድ ዓለም በየጊዜው እየታደሰችና እየተለወጠች ትሄዳለች ማለት ነው።

የጀርመኑ ሄግል ከላይ የተጠቀሰውን ዘዴ በሌላ መልኩ አስቀምጦታል። የመጀመሪያውን ሃሳብ ንጥር ሲለው ሁለተኛውን የንጥር ተቃራኒ እንግዲህ ከሁለቱ ተጨምቆ የሚወጣውን ደግሞ ተጨባጭ ብሎታል። ይህ የሄግል 3ቱ ቀመር ተብሎ ይታወቃል ፦- ንጥር- የንጥር ተቃራኒ - ተጨባጭ ።

ለምሳሌ የህልውናን ዲያሌክቲክስ ሲገልጽ ፡ በመጀመሪያ ህልውናን በነጠረ ህልው ስናስቀምጥ ከባዶ ነገር ጋር ምንም ልዩነት የለውም ። ሁሉም ወደ መኖር የሚመጣ ነገር በሙሉ ወደ አለመኖር እየተጓዘ መሆኑን ስንረዳ (ለምሳሌ መኖርም መሞት እንደሆነ ስንረዳ) ያንጊዜ ህልውናና ባዶነት በመዋሃድ መሆን ይሆናሉ። በዚህ ምክንያት መሆን የ ንጥር ህልውና የሚያስከትለውን የባዶነት ተቃርኖ ያረግባል ማለት ነው።

የካርል ማርክስ ዲያሌክቲክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሮዘንፌልድ ዲያሌክቲክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጠቃለያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]