Jump to content

ደልበህ

ከውክፔዲያ
(ከዴልባኤጥ የተዛወረ)

ደልበህአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቱዋጣ ዴ ዳናን ወገን የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። አባቱ ኦግማ ሲሆን ቀዳሚውንና አያቱን የኦግማ አባት ዳግዳን ለዙፋኑ ተከተለው። ደልበህ ለ፲ ዓመታት እንደ ነገሠ ይዘገባል።

ሌቦር ገባላ ኤረን ዘንድ፣ ከ፲ ዓመታት በኋላ ደልበህና ልጁ ኦሎም በካይኸር፣ የናማ ልጅ፣ የነኽታን ወንድም ተገደሉ፤ ከዚያ የደልበህ ሌላ ልጅ ፍያካ ማክ ደልበህ ካይኸርን ገደለውና ለከፍተኛ ንጉሥነት ተከተለው።

ደግሞ የደልበህ ፮ ወንድ ልጆች «ኦሎም፣ ፍያካ፣ ኢንዱይ፣ ብሪያን፣ ዩኻርባ፣ ዩኻር ነበሩ፤ የደልበህም ሴት ልጅ ዶናን የመጨረሻ ፫፣ የብሪያን፣ የዩኻርባና የዩኻር እናት ነበረች። እነዚህ ፫ እንደ ዳኑ አማልክት ተቆጠሩ፣ የ፫ አማልክት ተራራም ከነርሱ ተሰየመ። ያውም ደልበህ ደግሞ ቱይሪል ቢክሬዮ ተባለ።» በሌሎች ምንጮች ብሪያን፣ ዩኻርባና ዩኻር የቱይራን ልጆች ሲባሉ፣ ስለዚህ ደልበህና ቱይራን አንድ ግለሠብ እንደ ንበሩ ይታሥባል። «ቱዋጣ ዴ ዳናን» የሚለው የወገን ስያሜ ከነዚህ ፫ «ዳኑ»ና እና እናታቸው ዶናን ወይም ዳናን እንደ መጣ ይባላል። ሌቦር ገባላ ኤረን ደግሞ የደልበህ ሌላ ሴት ልጅ ቦይንድ ይጠቅሳል።

በኋላ የተጻፉት የአራት መምህሮች ዜና መዋዕልየአይርላንድ ታሪክ እንደሚሉት ግን፣ ደልበህ በገዛው ልጁና ተከታዩ በፍያካ ዕጅ ተገደለ።

ቀዳሚው
ዳግዳ
አይርላንድ (ባንባ) ከፍተኛ ንጉሥ
1354-1344 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ፍያካ ማክ ደልበህ